የመንግስታቱ ድርጅት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር በኢትዮጵያ ያደረጉት ጉብኝት የተሳካ ነበር – የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘይድ ራል ሁሴን  በኢትዮጵያ ያደረጉት ጉብኝት የተሳካ እንደነበር የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ አለም ተናግረዋል፡፡

አቶ መለስ በመግለጫቸው እንደጠቆሙት ኮሚሽነሩ በቆይታቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አህመድ ጋር በሃገሪቱ ባለው የሰብዓዊ መብት አያያዝ እና ዴሞክራሲ ዙሪያ መምከራቸውን ጠቁመዋል፡፡

ኮሚሽነር ዘይድ ኢትዮጵያ አዲስ ዴሞክራሲን ለመጀመር በአዲስ መንፈስ እየሰራች እንዳለች እና ዜጎቿም በመነቃቃት ስሜት ላይ እንደሚገኙ መታዘባቸውን እንደገለጹ አቶ መለስ ተናግረዋል፡፡

በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት አያያዝ ማዕከል ለመክፈት 17 የአፍሪካ ሃገራትን የሚያካትት የመግባቢያ ሰነድ መፈረሙም በመግለጫው ተጠቁሟል፡፡

የባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በኢትዮጵያ ያለው የሰብዓዊ መብት አያያዝ እንዲሻሻል የተለያዩ የአቅምና የቴክኒክ ድጋፎችን እንደሚያደርግ ኮሚሽነሩ ቃል መግባታቸውም ታውቋል፡፡