ኢህአዴግ በአልጀርስ ስምምነት ጉዳይ ያሳለፈው ውሳኔ በመቃወም የዓዲግራት ህዝብ ሰልፍ አካሄደ

ኢህአዴግ በአልጀርስ ስምምነትን ያለቅድመ ሁኔታ መቀበሉን ያሳለፈው ውሳኔ በመቃወም የዓዲግራት ህዝብ ሰላማዊ ሰልፍ ዛሬ በከተማው አውራ ጎዳናዎች ላይ አካሂዷል ፡፡
ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ ትናንት ባወጣው የአቋም መግለጫ፤የኢትዮጵያና የኤርትራ ጉዳይ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ በከፍተኛ የሀገር ፍቅር መስዋእትነት የከፈለበት ከህዝብ ጋር በቂ ውይይት ሳይደረግበት በኢህአዴግ በስራ አስፈጻሚ ብቻ ታይቶ እያለ እንዳለቀለት ተደርጎ በሚድያ ማስተላለፍ ጉድለት መሆኑ ነው የተመለከተው ፡፡

በዚሁም የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ በሄረሰቦችና ህዝቦች ሳይወያዩበት መሆኑ በህዝቡ ዘንድ ቅሬታ፣ቁጣንና መደናገርን መፍጠሩን ነው ከህወሓት ድረ ገጽ የተገኘው መረጃ የተጠቀሰው ፡፡

ዋልታ በስልክ ያነገጋራቸው በሰላማዊ ሰልፉ የተገኙት የኢሮብ ብሄርሰብ ተወላጆች በሰጡት አስተያየት፤ በቅርቡ የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ያስተላለፈውን ውሳኔ ለመወቃወም ሰልፍ መውጣታቸውን ገልጸዋል፡፡

ተቃውሞአቸውን ለዓዲግራት ከተማ የገለጹት ተወላጆቹ ውሳኔው ህዝብን ያመከለ ባለመሆኑ ኢህአዴግ ጉዳዩን እንደገና ማጤን እንዳለበትም አመልክተዋል ፡፡