መንግስት ከ300 በላይ እስረኞች በይቅርታ እንዲፈቱ ወሰነ

የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ በእስር ላይ የነበሩ 304 የህግ ታራሚዎች በይቅርታ እንዲፈቱ ወስነዋል።

የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ይቅርታ የተደረጉ ታራሚዎች ከሞት እስከ እድሜ ልክ የተፈረደባቸው እንደነበሩ አስታውቋል።

በይቅርት እንዲፈቱ ከተወሰኑ መካከል 289ኙ በሽብርተኝነት ወንጀል ተከሰው የተፈረደባቸው ሲሆኑ ዘጠኙ የሞት ፍርድ ተፈርዶባቸው የነበሩ ሶስቱ ደግሞ የረጅም ጊዜ ፍርድ ተወስኖባቸው በማረሚያ ቤቱ የቆዩ መሆናቸው ተመልክቷል።

በይቅርታ ከተለቀቁት መካከልም ሶስቱ የኬንያ ዜግነት ያላቸው ሲሆን ይህም ከኬንያ መንግስትና ህዝብ ጋር ያለውን መልካም ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር ያለመና በኬንያ ታስረው የነበሩ ዜጎቻችን መፈታትን ታሳቢ ያደረገ እንደሆነም ነው ጠቅላይ አቃቤ ህግ በመግለጫው ጠቁመዋል።

ከቃሊቲ ማረሚያ ቤት ከወጡት እስርኞች መካከል የአካል ጉዳትና የጤና እክል ያለባቸው እንዳሉ ተጠቁማል።

በተመሳሳይ በክልል ያሉ እስረኞችም ከሰኞ ሰኔ 11 ቀን 2010 ጀምሮ እንደሚፈቱም ተገልጸዋል።

መንግስት የኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በ17 ቀናት ባደረጉት ስብሰባ በደረሰባቸው ውሳኔዎችና በአስቀመጠው አቅጣጫዎች መሰረት የተለያዩ እርምጃዎች ሲወስድ ቆይቷል።

በተለያዩ ምክንያቶች ተከሰው በእስር ላይ የነበሩ ታራሚዎችና በክስ ሂደት ላይ የቆዩ ክሳቸው ተቋርጦ መፈታታቸውም ይታወሳል።