ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል የደኢህዴን ሊቀመንበር በመሆን ተመረጡ

የህዝብ  ተወካዮች ምክር ቤት  አፈጉባኤ  በመሆን  እያገለገሉ የሚገኙት ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል የደኢህዴን ሊቀመንበር ሆነው ተመረጡ፡፡

የደኢህዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ  የደኢህዴን ሊቀ መንበር አቶ ሽፈራው ሽጉጤ በራሳቸው ፈቃድ ሥልጣን መልቀቃቸውን ተከትሎ ዛሬ ባካሄደው ምርጫ ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚልን በሊቀመንበርነት መርጧል፡፡

 አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ከደኢህዴን ሊቀመንበርነትና ሥራ አስፈጻሚነት በመልቀቅ  የደኢህዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ  አባል ሆነው  እንደሚቀጥሉ  ቀደም ሲል በቀረበው  ዜና  ተመልክቷል  ።