ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የኤርትራ የልዑካን ቡድንን ተቀበሉ

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የኤርትራ የልዑካን ቡድንን በቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ ተቀበሉ ተቀበሉ፡፡

ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በተናገሩት መሰረት በሁለቱ አገሮች ግንኙነት ላይ የሚመክር እና ከፍተኛ ባለሥልጣናት የተካተቱበት ቡድን አዲስ አበባ ደርሷል፡፡
የልዑካን ቡድኑን የፕሬዝዳንቱ አማካሪ እና የፖለቲካ ጉዳዮች ሃላፊ የማነ ገብረአብ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳላህ መርተውታል፡፡
በአቀባብሉ ላይ በኢትዮጵያ በኩል ከጠቅላይ ሚኒስትሩ በተ ጨማሪ  ከፍተኛ የመንግስት ሃላፊዎች ፣አርቲስቶች፣ አትሌቶች እና የሃይማኖት አባቶች ተገኝተዋል፡፡
የልዑካን ቡድኑ አዲስ አበባ የገባው የኢህአዲግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የአልጀርሱን ስምምነት ያለ ቅደመ ሁኔታ እንደሚቀበል ማስታወቁን ተከትሎ ባቀረበው ጥሪ መሰረት ነው፡፡