ሜጀር ጄነራል ደግፌ በዲ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው ተሾሙ

ሜጀር ጄነራል ደግፌ በዲ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው ተሾመዋል።

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ዘይኑ ጀማል ለዋልታ እንደገለጹት፤ ሜጀር ጄነራል ደግፌ የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነዋል።

ከዚህም በተጨማሪ ረዳት ፖሊስ ኮሚሽነር ሀሰን ነጋሽ እና አቶ ዘላለም መንግስቴ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ተደርገው መሾማቸውን ጠቁመዋል።