ሲራጅ ፈጌሳ የደኢህዴን ምክትል ሊቀመንበርነታቸውን በፈቃዳቸው ለቀቁ

የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢህዴን) ምክትል ሊቀመንበር ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩት አቶ ሲራጅ ፈጌሳ ከኃላፊነታቸው በገዛ ፈቃዳቸው ለቀቁ።

ደኢህዴን አቶ ሚሊዮን ማቴዎስ የደኢህዴን ምክትል ሊቀመንበር ሆነው መመረጣቸውን የንቅናቄው ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋዬ በልጂጌ ተናግረዋል።

አቶ ሲራጅ ደኢህዴንን 1980 ጀምሮ በአባልነት የተቀላቀሉ ሲሆን፣ በኋላም የፓርቲው ስራ አስፈጻሚና ማዕከላዊ ኮሚቴ፣ በአሁኑ ወቅት ደግሞ የንቅናቄው ምክትል ሊቀመንበር ሆነው እያገለገሉ ነበር።

አቶ ሲራጅ የስልጤ ዞን አሰተዳዳሪ ሆነው ያገለገሉ ሲሆን ኢህአዴግ  1997ቱን ምርጫ ማሸነፉን ተከትሎ የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትር ሆነው ተሾመዋል።

2001 እስከ 2010 . ደግሞ የመከላከያ ሚኒስትር ሆነው ሰርተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ባዋቀሩት አዲስ ካቢኔ ውስጥም የትራንስፖርት ሚኒስትር ሆነው እያገለገሉ ይገኛሉ።