በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል የተጀመረው ግንኙነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ጠየቁ

በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መካከል የተጀመረው ግንኙነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ጠየቁ፡፡

ለዋልታ አስተያየታቸውን የሰጡ የከተማዋ ነዋሪዎች በሁለቱ ሀገራት መካከል የተጀመረው መልካም ግንኙነት ለማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ትስስር ያለው ፋይዳ የጎላ ነው ብለዋል፡፡

ከዚህ በፊት በተፈጠረው አለመግባባት ሁለቱ ወንድማማች ህዝቦች ተለያይተው የቆዩ ቢሆንም አሁን በተፈጠረው የሰላም  ሂደት ደስተኛ እንደሆኑና ከኤርትራዊያን ቤተሰቦች ጋር ለመገናኘት እንደተዘጋጁ ተናግረዋል፡፡

የሁለቱ ሀገራት ህዝቦችን የሚያመሳስሉ በርካታ ነገሮች ያላቸው መሆኑን የተናገሩት ነዋሪዎች በተፈጠረው ሰላም የማስፈን ሂደቶች የበኩላቸውን ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

ከኢትዮጵያ በኩል የቀረበውን የሰላም ጥሪ የኤርትራ መንግስት በአዎንታዊ መልኩ በመቀበል ልዑካን ቡድን መላኩ እንዳስደሰታቸውም ነዋሪዎቹ ተናግረዋል፡፡