በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል አሁን እየተካሄደ ያለውን የሰላም ሂደት ኢጋድ አደነቀ

የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት /ኢጋድ/ ዋና ፀሃፊ አምባሳደር ማህቡብ ማዓሊምእናደሉት የኤርትራ ከፍተኛ የልዑክ ቡድን ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ከኢትዮያ መንግስት ጋር በመወያየታቸው ኢጋድ እንደሚያደንቅ ገልፀዋል፡፡

ከሁለት አስርት ዓመታት በኋላ ሁለቱ መንግስታት እና ህዝቦች መካከል ተቋርጦ የነበረው ግንኙነት ዳግም መመለሱ ኢጋድን እንዳስደሰተው ተናግረዋል፡፡

አምባሳደሩ እንዳሉት ሁለቱ ሀገራት በርካታ የሚያቀራርቡ የጋራ ጉዳይ ያላቸው በመሆኑ ግንኑነታቸውን ሰላማዊ በሆነ መንገድ ዳግም ማደስ እንደሚገባቸው ገልፀዋል፡፡

ዋና ፀሃፊው አክለውም በኢትዮጵያ በኩል የቀረበውን የሰላም ጥሪ የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፍወርቂ ለሰጡት አወንታዊ ምላሽ አድናቆት ለግሰዋል፡፡