የሶማሌ ክልል በቦምብ ጥቃቱ ለተጎዱ ዜጎች የ15 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ወደ ኃላፊነት ከመጡ ወዲህ ላመጡዋቸው ለውጦች ድጋፍ እና እውቅና ለመስጠት በተደረገው ሰልፍ ላይ በቦምብ ጥቃት ለተጎዱ ዜጎች የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል 15 ሚሊየን ብር ለግሷል።

የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግስት የስራ አስፈጻሚ አባላት ባካሄደው የአስቸኳይ ጊዜ ስብስባ በአዲስ እበባ መስቀል አደባባይ ባሳለፍነው ሰኔ 16 የድጋፍ ሰልፍ ላይ በቦንብ ፍንዳታ ለተጎዱ ሰዎች 15 ሚሊየን ብር መለገሱን ነው የተገለጸው።

የኢትዮ ሶማሌ ክልል ህዝብ በንጹሃን ዜጎች ላይ የተደረገውን የቦንብ ጥቃት በማውገዝና የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድን በመደገፍ ባሰለፍነው እሁድ በጅግጅጋ ከተማ የድጋፍ ሰልፍ ማድረጉም ይታወሳል።