የለውጥ አመራሩ እና ምሁራን ሃሳብ የሚለዋወጡበት መድረክ ሊጠናከር ይገባል- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስተር አቶ ደመቀ መኮንን

በሃገሪቱ የሚታየውን ለውጥ የሚመራው አመራር እና ምሁራን ሃሳብ የሚለዋወጡበት መድረክ ሊጠናከር እንደሚገባ  ምክትል ጠቅላይ ሚኒስተር አቶ ደመቀ መኮንን ገልጸዋል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን የተናገሩት በመለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ አዘጋጅነት ለሁለተኛ ጊዜ ሃገር አቀፍ የምርምር ኮንፍረንስ በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አዳራሽ እየተካደ ባለበት ወቅት ነው፡፡

በመድረኩ ላይ ምሁራን፣ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች፣ የህዝብ ተወካዮች እና የፌደሬሽን ምክር ቤት ተወካዮች እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡