የደቡብ ሱዳን ተቀናቃኞች በመጪዎቹ አራት ወራት የሽግግር መንግስት ለማቋቋም ተስማሙ

የደቡብ ሱዳን ተቀናቃኞች በመጪዎቹ አራት ወራት ውስጥ የሽግግር መንግስት ለማቋቋም ተስማምተዋል፡፡

በምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ኢጋድ ጣልቃ ገብነት በሱዳን ካርቱም ሁለቱ ሀይሎች ማለትም ፕሬዝዳንት ሳልቫኪርና የቀድሞ ምክትላቸው ዶክተር ሪክ ማቸር ከ72 ሰዓታት ብኋላ የሚተገበር የተኩስ አቁም ስምምነት መፈራረማቸው የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ለሰላማቸው ዋጋ የሰጡ መሆኑን ያስመሰከረ አስብሎለታል፡፡

እንደ አልጀዚራ ዘገባ ጉዳዩን በማሸማገል ከፍተኛ ሚናን የተወጣችው ካርቱምም ነፃነቷን ለቀዳጀችው ደቡብ ሱዳን ወንድም ሀዝብ ድንበሯን ክፍት እንደምታደርግ ይዞ መውጣቱ በአፍሪካ ቀንድ ለረገበው ሰላም ሌላ ማሳያ እንደሆነ አመላክቷል፡፡

የተኩስ አቁም ስምምነቱ ለደቡብ ሱዳን ግጭት መቋጫ ከመሆኑም በላይ አዲስ ምዕራፍን ይከፍታል ሲሉ ማቻር በስምምነቱ ወቅት ለጋዜጠኞች  ተናግረዋል፡፤

የሱዳኑ ፕሬዝዳንት አልበሺር የደቡብ ሱዳናውያን ስጦታ ያሉት ስምምነት የተሳካ እንዲሆን ሁለቱ ተቀናቃኞች በስልጣን ክፍፍል ላይ ጠለቅ ያለ ውይይት ማድረግ ይኖርባቸዋል ማለታቸውን ሮይተርስ የካርቱምን የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ አልዲርዲር መሀመድን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡

አሁን በስምምነቱ መሰረት የተራዶ ድርጅቶች እንደልብ ተንቀሳቅሰው መስራት እንዲችሉና እስረኞችን መልቀቅ፤ የመንግስትና የተቀናቃኝ ሀይል ወታደሮች የያዙትን ግዛት ለቅው እንዲወጡ ያስገድዳል፡፡

ስምምነቱን ወደ ተግባር በሚለወጥበት ሂደት ዙርያ በአራት ወራት ውስጥ የሽግግር ምንግስት ተቋቁሞ ከሶስት አመታት ብኋላ ለሚደረገው ምርጫ ቅደመ ዝግት እንዲያደርግ ሁለቱ ሃይሎች ከመግባባት የደረሱበት ነጥብ ሆኗል፡፡

ምልባትም እንደስጋት የተነሳው ጉዳይ ማቻር በሳልቫኪር አስተዳደር ለመስራት ፍቃደኛ አለመሆን ከዚህ ቀደም የሚነሳ መሆኑን ተከትሎ፤ ባሁኑ ደግሞ ለስልጣን ክፍፍል ሲባል ጁባ ሶስት ዋና ከተሞች እነዲኖራት የሚለውን ሀሳብ ማቻር እንደማይቀበሉት መግለፃቸው ቀጣይ ድርድር እንደሚሻ አመላካች ሆኗል፡፡

ደቡብ ሱዳን አንድ ሀገር ሆና ሳለ ለሶስት መከፋፈሉ ተገቢ እንዳልሆነ የሚያነሱት የማቻር ቃል አቀባይ ጋራንግ ማቢዮር ምንም አይነት የውጪ ሀይል በጁባ ምድር እንዲሰማራ ፍላጎት እንደሌላቸው አስረድተዋል፡፤

ሁለቱ መሪዎች አንደ አውሮፓውያን አቆጣተር በ2015 ተኩስ ለማቆም ስምምነት ቢፈራረሙም ህጉን ጥሰው ወደ እርስ በርስ ጦርነት መግባታቸው አይዘነጋም፡፡ በዚህ ሳቢያም ግጭቱ ሰባት ሚሊዮኖቹን ለአስቸኳይ የምግብ እርዳታ እንደዳረጋቸው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት መረጃ ያመለክታል፡፡

እንደ አለም ባንክ አሀዝ ደግሞ ጁባ ነፃነቷን በተቀዳጀች ማግስት ዋነኛ የምጣኔ ሀብት የጀርባ አጥንት የሆነው የነዳጅ ሀብት 98 በመቶ አመታዊ እድገቷን ይዶግም ነበር፡፡ ሆኖም በቀን ታመርት ከነበርው 350 ሺ ወደ120 ሺ በርሜል ማሽቆልቆሏ ገቢውን ከሚመዘብሩት ሙሰኞች ተደምሮ ለደቡብ ሱዳን ክፉኛ የራስ ምታት ሆኖባት ቆይቷል፡፤

በያዝነው ወር ከርቱምና ጁባ በጦርነት የተጎዶ የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመራቸውን ዳግም ለመጠገን መስማማታቸው የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ወደነበረበት ከመመለሱም ባሻገር የጁባን ምጣኔ ሀብት በመጠገን ረገድ ጉልህ ሚና አንደሚኖረው ተዘግቧል፡፡

የተጀመረው የሁለቱ መሪዎች ድርድር በቀጣይ በኬኒያ ናይሮቢ ከተደረገ በኋላ በመጨረሻም መቋጫውን በአዲስ አበባ ያገኛል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ (አልጀዚራና ሮይተርስ)