የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርና ስቴም ሲነርጂ ወጣቶችን ወደ ፈጠራ ለማስገባት የሚያስችል ሥራን ለማካሄድ የጋራ ስምምነት ፈጸሙ

የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከስቴም ሲነርጂ ጋር በትምህርት ላይ ያሉ ወጣቶች ወደ ፈጠራ ስራ እንዲገቡ ለማድረግ በጋራ ለመስራት ሰምምነት ተፈራርመዋል፡፡

ስምምነቱን የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ዴኤታ ሹመቴ ግዛው (ዶ/ር) መቀመጫውን አሜሪካ ሀገር ካደረገው ከስቴም ሲነርጂ ኤክስኩቲቭ ዳይሬክተር ወ/ሮ ቅድስት ገብረ አምላክ ጋር ፈርመዋል፡፡

በስምምነቱ እንደተገለጸው በትምህርት ላይ ያሉ ወጣቶች በሂሳብ፣ በሳይንስ፣ በቴክኖሎጂና ኢንጂነሪንግ ዘርፍ ወደ ፈጠራ እንዲገቡ ለማድረግ ይሰራል፡፡

በፈጠራ ማዕከል ግንባታ ላይ በጋራ እየሰሩ ሲሆን ወጣቶች የሳይንስ ሰው እንዲሆኑ ለማድረግ እንደሚሰራ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ዴኤታ ዶክተር ሹመቴ ግዛው ገልጸዋል፡፡ (ምንጭ፤ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር)