ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ፈረንሳይ ገቡ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ፈረንሳይ ገብተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ባደረጉላቸው ጥሪ መሠረት ነው ፓሪስ ፈረንሳይ የገቡት፡፡

ሁለቱ መሪዎች በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የሚመክሩ ሲሆን በተለይም በአፍሪካ ቀንድ የጸጥታ ሁኔታ፣ በኢትዮጵያ በመካሄድ ላይ ስላለው ሪፎርም፣ በንግድ እና ኢንቨስትመንት ዙሪያ እንደሚወያዩ ይጠበቃል ሲል የጠቅላይ ሚኒስትር ልዩ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፍጹም አረጋ አስታውቋል፡፡