ፖሊስ በእነ አብዲ ኤሌ የክስ መዝገብ ላይ የጠየቀውን ተጨማሪ 14 የምርመራ ቀናት ፍርድ ቤቱ ፈቀደ

የፌደራል ፖሊስ መርማሪ ቡድን በእነ አብዲ ኤሌ የክስ መዝገብ የጠየቀውን ተጨማሪ የ14 የምርመራ ቀናት ፍርድ ቤቱ ፈቀደ ።

በእነ አብዲ ኤሌና ተጠርጣሪዎች የክስ መዝገብ በዛሬው ዕለት የተመለከተው  የልደታ ፍርድቤት በሶማሌ ክልል ሄጎ በተባለው ቡድን ዘር ቀለምና ኃይማኖትን በመለየት   ከሐምሌ 26 እስከ 30 ፣ 2010 ዓም ድረስ በ200 ሰዎች ላይ ወንጀል በመፈጸም የተጠረጠሩትን የቀድሞ የሶማሌ  ክልል ፕሬዚዳንትና ሌሎች ተጠርጣሪዎች ጉዳየ ለማጣራት ተጨማሪ ቀናት ጠይቋል።

ፖሊስ ባለፉት በተሠጡት 10 ቀናት ውስጥ የግድያ ወንጀል  ተፈጽሞባቸዋል  የተባሉት ከ200 በላይ ሰዎችን አስከሬን  በማውጣት  ጭምር ምርመራ  እያደረገ  መሆኑን  በችሎቱ  ገልጿል

እንዲሁም  በተጨማሪ  በቀብሪ ደሃር ፣ ጎዴና ሌሎች አካባቢዎች ላይ ጉዳት የደረሰባቸው  62 ሰዎች የህክምና  ማስረጃ ከሶማሊኛ ወደ  አማርኛ  የመተርጎም ሥራ መከናወኑን ፖሊስ  ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል ።

በጅግጅጋ ከተማ  አካባቢ በተፈጠሩት ሁከቶች ሆን ተብሎ መብራት  እንዲጠፋ በማድረግ የአጥፊዎቹ ማንነት  እንዳይታወቅ  መደረጉን ፖሊስ  በምርመራ ሂደቱ ማጣራቱን  ገልጿል።

የፌደራል ፖሊስ  የምርመራ ቡድን ፍርድ ቤቱ  ተጨማሪ የ10 ቀናት ጊዜ  የጠየቀውም   እስከሬናቸው የተገኙ 200 ሰዎችን ማንነት ለመለየት ፣ ተጨማሪ የምስክር ቃል ለመሰብሰብ ፣ ጉዳት የደረሰባቸውን  የ37 ሰዎች የእንግሊዘኛ ሰነድ  ለመተርጎም፣ የጦር መሣሪያና ህገ ወጥ ገንዘብን የመሰብሰብ ሥራዎች ባለማለቃቸውን መሆኑን ለፍርድ ቤቱ በዝርዝር አስረድቷል ።

የቀድሞ  የሶማሌ ክልል ፕሬዚደንት  ጠበቆች በበሉላቸው ተጨማሪ የምርመራ  ጊዜ  መጠየቅ  እንደሌለበትና  የተጠርጣሪው  የዋስትና  መብት ሊከበር  እንደሚገባ ቢጠይቅም  በፍርድ ቤቱ ውድቅ ተደርጓል ።