የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢትዮጵያን የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ስምምነት አባልነት አፀደቀ

የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢትዮጵያን የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ስምምነት አባልነት አፀደቀ።

ምክር ቤቱ ስምምነቱን ዛሬ ባካሄደው ስብሰባው ያጸደቀ ሲሆን ስምምነቱ የዓለም የንግድ ድርጅት ከተመሠረተ ትልቁ የንግድ ስምምነቶች አንዱ ሲሆን፥ በአፍሪካ አንድ ገበያ ለመፍጠር ሙከራ ያደርጋል።

ውሳኔው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከሚያራምዱት አዕምሮን ለሃሳብ መንሸራሸርና ገበያዎች ለትስስር በመክፈት በአፍሪካ ክልላዊ ውህደትንና ጥብቅ ጥምረት እንፍጠር ከሚለው ራዕይ ጋር ይጣጣማል።

የኢትዮጵያ ውሳኔና የፓን አፍሪካን እሳቤ የመደገፍ ታሪካዊ ልምድ የአፍሪካን ውህደት በተሻለ ሁኔታ ወደ እውነታነት ያስጠጋል። (ምንጭ፡- የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት)