ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር እየተወያዩ ነው

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር እየተወያዩ ነው፡፡

የውይይት መድረኩ ከጥቂት ወራት በፊት በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ጋባዥነት ከተደረገው የቀጠለ ነው ተብሏል፡፡

የዛሬውን ውይይት አስተባባሪ ከሆኑት አንዱና የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ የሺዋስ አሰፋ እንደተናገሩት የመድረኩ ዋና አላማ በዚህ የፖለቲካው ሽግግር ወቅት የፖለቲካ አመለካከትን በሰላማዊ መንገድ መለዋወጥ ልምድን ለማሰደግ ነው።

ውይይቱ ታሪካዊና በኢትዮጲያ የፖለቲካ ታሪክና ትርክት ውስጥ አይነተኛ ሚና አለውም ተብሏል፡፡

በመድረኩ ከአራት የፖለቲካ ድርጅት አመራሮችም የውይይት ጽሁፍ ይቀርባል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ (ምንጭ፡-የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት)