እነሜጄር ጀኔራል ክንፈ ዳኘዉ ያቀረቡትን ክስ መቃወሚያ ፍ/ቤቱ ዉድቅ አደረገዉ

ሜጄር ጀኔራል ክንፈ ዳኘዉና ሌሎች አስር የሜቴክ የስራ ሃላፊዎች እንዲሁም ባለሀብቶች በሆቴሎችና ፒቢሲ ግዥ መንግስትን የ436 ሚሊዮን ትርፍ አሳጥታችኋል በሚል የቀረበባቸዉ ክስ ላይ ያቀረቡት መቃወሚያ በፍ/ቤቱ ዉድቅ ተደረገ፡፡

ወንጀሉን አልፈፀምንም በማለታቸዉ አቃቤ ህግ ያስመዘገባቸዉን 12 ምስክሮች እንዲያሰማ የከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 15ኛ ወንጀል ችሎት ከመጋቢት 30 ጀምሮ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

በሁለት ክስ ጥር 7/ 2011 ሜጀር ጀኔራል ክንፈ ዳኘዉን ጨምሮ የግዥ ኮሚቴ አባል በመሆን የሰሩትን ልሎች የተቋሙ ሃላፊዎች እንዲሁም ባለሃብት አቶ አለም ፍፁም ሪቬራ ሆቴልንና አንድ የፒቢሲ ፋብሪካ በተጋነነ ዋጋ በመሸጥ በመንግስትን የ415 ሚልዮን ብር አሳጥታችኋል በሚል ወንጀል ተጠርጥረዉ መያዛቸዉ ይታወሳል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ከኢምፔያል ሆቴል ሽያጭ ጋር በተያያዘ አቶ ኤርሚያስ አመልጋ መንግስትን 21 ሚሊዮን ብር በማሳጣት ተከሰዋል፡፡