የሕዋስ ንቅለተከላ ህክምና የኤችአይቪ ህሙማን መፈወሱ ተገለጸ

በብሪታኒያ በተደረገ የሴል ንቅለተከላ ህክምና የኤችአይቪ ህሙማን መፈወሱ ተገለጸ፡፡

በስም ያልተጠቀሰ የቫይረሱ ተጠቂን ከቫይረሱ ነፃ ያደረገው ለደም ካንሰር የተደረገለት የሴል ንቅለተከላ ህክምና መሆኑ ተገልጿል፡፡

ይህ ውጤት የተገኘውም በሀገሪቱ ለሁለተኛ ጊዜ በተከናወነው የሴል ንቅለተከላ ህክመና  ነው ተብሏል፡፡

ከዛሬ 18 ወራት በፊት የፀር ቫይረስ መድሃኒቱን መውሰዱን እንዳቋረጠ የተነገረው ይህ ሰው በደሙ ውስጥ ቫይረሱ እንደሌለ ተረጋግጧልም ነው የተባለው፡፡

በአውሮፓዊያኑ 2012 ለደም ካንሰር የተጋለጠው በሽተኛው ከ2003 ጀምሮ ቫይረሱ በደሙ ውስጥ እነደነበረበትም ተነግሯል፡፡

በዚህም የኬሞቴራፒና የሴል ንቅለ ተከላ ከተደረገለት በኋላ ከሁለቱም በሽታዎች መፈወሱ በዘገባው ተመላክቷል፡፡

የለንደን ዩኒቭርሲቲ ኮሌጅ፣ የለንደን ኢምፐሪያል ኮሌጅ፣ የካምፕሪጅ ኮሌጅና የኦክስፎርድ ዩንቨርሲቲ ተማራማሪዎች በህክመናው ላይ እንደተሳተፉም ተገልጿል፡፡

(ምንጭ፡- ቢቢሲ)