የደኢህዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ልዩ ስብሰባውን እያካሄደ ነው

የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክሪያሲያዊ ንቅናቄ (ደኢህዴን) ማዕከላዊ ኮሚቴ ልዩ ስብሰባውን ማካሄድ ጀመረ፡፡

የደኢህዴን ሊቀ መንበርና የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈርያት ካሚል ልዩ ስብሰባው ሀገራዊና ክልላዊ የጸጥታና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ዙሪያ እንደሚወያይ ተናግረዋል፡፡

በማዕከላዊ ኮሚቴው ልዩ ስብሰባ የተለያዩ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት እንደሚካሄድባቸውም ተጠቁሟል፡፡

ልዩ ስብሰባው በአዲስ አበባ እየተካሄደ ሲሆን፣ ለሶስት ቀናት ይቆያልም ነው የተባለው፡፡