አክራ የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና ሴክሬታሪያት ዋና መቀመጫ ሆና ተመረጠች

የአፍሪካ ህብረት የአስፈፃሚው ምክር ቤት አክራን የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና ሴክሬታሪያት ዋና መቀመጫ አድርጎ መረጠ፡፡

የኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የሚመራው ልዑካን ቡድን በኒያሚ-ኒጀር እየተካሄደ በሚገኘው የአፍሪካ ህብረት የአስፈፃሚው ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ላይ በመተሳፍ ላይ ይገኛል።

ምክር ቤቱ በዛሬው ውሎ ባካሄደው ስብሰባ የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና ሴክሬታሪያት ዋና መቀመጫ ምርጫ የጋናዋ ዋና ከተማ አክራ አስተናጋጅ እንድትሆን መርጠዋል።

ምክር ቤቱ በመቀጠልም የተለያዩ ምርጫዎችን በማካሄድና የተለያዩ ውሳኔዎችን በማፅደቅ ዛሬ ማምሻውን እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል።

12ኛው አስቸኳይ የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ እ.ኤ.አ ጁላይ 7 ቀን 2019 ፤ እንዲሁም የመጀመሪያው የክልላዊ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ ሊቀመንበር አገራት ቅንጅታዊ ስብሰባ እ.ኤ.አ ጁላይ 8 ቀን 2019 ዓ.ም በኒያሚ-ኒጀር እንደሚካሄድ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃልአቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡