የአዋሽ-ኮምቦልቻ-ሀራ ገበያ የባቡር መስመር ዋሻ ግንባታ ተጠናቀቀ

ኮምቦልቻ፣ሐምሌ 30/2008(ዋኢማ)- በግንባታ ላይ የሚገኘው የአዋሽ-ኮምቦልቻ- ሀራ ገበያ የባቡር መስመር የዋሻ ግንባታ የመጀመሪያ ምዕራፍ  ግንባታ ተጠናቀቀ፡፡

ትናንት አንድ ሺ 530 ሜትር ርዝመት ያለው የዋሻ ግንባታ መጠናቀቅን በማስመልክት በተዘጋጀው ሥነ ሥርዓት ላይ የኢኮኖሚና ልማት ትብብር ሚኒስትር ዴኤታ አህመድ ሽዴ እንደተናገሩት የባቡር ፕሮጀክት አጠቃላይ ሥራ 45 በመቶ ተጠናቋል፡፡

የባቡሩ መስመር መዘርጋት የሰሜን ምስራቅ የአገሪቱን አካባቢዎች ከጅቡቲ ወደብ ጋር በቀላሉ ለማገናኘት እንደሚረዳ ሚኒስትር ዴኤታው ገልፀዋል፡፡

የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶክተር ኢንጂነር ጌታቸው በትሩ በበኩላቸው የአዋሽ-ኮምቦልቻ- ሀራ ገበያ የምድር ባቡር ፕሮጀክት 392 ኪሎ ሜትር እንደሚረዝም ተናግረዋል፡፡ግንባታውም የአውሮፓን የጥራት ደረጃ ጠብቆ እየተከናወነ እንደሆነ ነው የተናገሩት፡፡

የባቡር መስመር ፕሮጀክት በአጠቃላይ ሶስት ሺ 200 ሜትር የሚረዝሙ ስድስት ዋሻዎች እንደሚኖሩት ዶክተር ኢንጂነር ጌታቸው ገልፀዋል፡፡ ከዚህም ውስጥ አንድ ሺ 530 ሜትር የሚረዝመው የዋሻ ግንባታ ተጠናቋል፡፡ ለግንባታውም አንድ ነጥብ ሰባት ቢሊዮን ብር ወጭ

ፕሮጀክት ለሰውና ለዕቃዎች ማጓጓዥ እንደዲያገለግል በሚያስችል መልኩ ነው የተገነባው፡፡ ያፒ መርከዝ የተባለ የቱርክ ኩባንያ ግንባታውን እያከናወነ ሲሆን የፈረንሳዩ ቢስትራ ኩባንያ የማማከር ሥራውን እያከናወነ ይገኛል፡፡