የአሸንዳ በዓልን በዓለም ቅርስነት ለማስመዝገብ ጥረቱ ቀጥሏል

ነሐሴ 16/2008(ዋኢማ)-የአሸንዳ በዓልን በዓለም ቅርስነት ለማስመዝገብ የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ መቀጠሉን የትግራይ ክልል የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ አስታወቀ፡፡

የትግራይ ህዝብ የማንነት መገለጫና ትልቅ ባህላዊ ባህላዊ ዕሴት የሆነውን የአሸንዳ በዓል በቅርስነት የማስመዝገቡ ጥረት ጥሩ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የቢሮው ኃላፊ አቶ ገብረ ሚካኤል መለስ ተናግረዋል፡፡

ባለፈው ዓመት በተከበረው የአሸንዳ በዓል ላይ የዩኔስኮ አመራሮች መገኘታቸውን የገለፁት ኃላፊው የአሸንዳ በዓልን በዓለም ቅርስነት ለማስመዝገብ የሚያችል ምቹ ሁኔታ እንዳለ መገንዘባቸውን ተናግረዋል፡፡

ሴቶች በተለየ መልኩ ነፃነታቸውን የሚገልፁበት በዓል በዓለም ዓቀፍ ደረጃ እንደሌለ የዩኔስኮ አባላት ዕውቅና መስጠታቸውን አቶ ገብረ ሚካኤል ገልፀዋል፡፡

ይህ ዕውቅና በዓለም ዓቀፍ ደረጃ በቅርስነት ለማስመዝገብ በቂ ዝግጅት ተደርጓል ብለዋል-ኃላፊው፡፡ በዓሉ በዋናነት በመቀሌ የሚከበር ሲሆን በአክሱምና ዓብይ ዓዲ ከተሞች በድምቀት እንደሚከበር ነው ያስረዱት፡፡

የበዓሉን ሂደት ለመታዘብ ለመዘገብ አሶሼትድ ፕሬስ፣አናዶሉ፣ሮይተርስና ሲሲተቪን  የመሳሳሉ የመገናኛ ብዙኃን ተቋማት መቀሌ መግባታቸውን ኃላፊው ገልፀዋል፡፡ በዚህም ሂደቱን ለዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብ በስፋት ያስረዳሉ፡፡

የዩኔስኮ አባላት የሚሳተፉበት ትልቅ ዐውደ ጥናት የሚካሄድ ሲሆን የባህልና ቱሪዝምና ምሁራንም ይሳተፋሉ፡፡ በዚህ ላይ ስለ አሸንዳ ምንነትና ታሪካዊ አመጣጥ በስፋት እንደሚዳሰሰስ ኃላፊው ገልፀዋል፡፡

ከነሐሴ 15 እስከ ነሐሴ 25 2008 ዓ.ም የሚከበረው የአሸንዳ በዓል እየጸቀረፀ በዶክመነት ይያዛል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ከፍተኛ የዲፕሎማሲ ሥራ ይከናወናል፡፡ ሰፊ የማስተዋወቅ ሥራ እየተሰራ ነው፡፡በማህበራዊ ሚዲያዎችና በተለያዩ መገናኛ ብዙኃን የማስተዋወቅ ሥራ ይሰራል፡፡