ኦሮሚያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት በሀዋሳ፣ መቀሌ እና ባህርዳር ቅርንጫፎቹን ሊከፍት ነው

የኦሮሚያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት በሀዋሳ፣ መቀሌ እና ባህርዳር ከተሞች ቅርንጫፍ መስሪያ ቤቶችን ለመክፈት ዝግጅቱን ማጠናቀቁ ተገለፀ።

የኦሮሚያ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሀላፊ አቶ አዲሱ አረጋ እንዳስታወቁት፥ ድርጅቱ ቅርንጫፎቹን የሚከፍተው የኦሮሚያ ክልል ቅርንጫፎቹ ከሚከፈትባቸው ክልሎች ህዝቦች ጋር ያለውን ወንድማማችነት ለማጎልበት እንዲረዳው ነው።የ

የኦሮሚያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት በአሁኑ ወቅት በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋዎች ስርጭት እንዳለው ይታወቃል።

ድርጅቱ በቀጣይም በሌሎች የሀገሪቱ ቋንቋዎች ስርጭት ለመጀመር በዝግጅት ላይ መሆኑን አቶ አዲሱ ገልፀዋል-  (ኤፍ.ቢ.ሲ.)።