ሩሲያና ሳውዲአረቢያ የድፍድፍ ነዳጅ የገበያ ዋጋን ለማረጋጋት ተስማሙ

ሩሲያና ሳውዲአረቢያ በቀን የሚመረተውን የድፍድፍ ነዳጅ ምርትን በመቀነስ  የነዳጅ የገበያ ዋጋን ለማረጋጋት መስማማታቸው ተገለጸ ።  

ሩሲያና ሳውዲ አረቢያ የድፍድፍ ነዳጅን የገበያ ዋጋ ለማረጋጋት እኤአ  እስከ መጋቢት 2018 ድረስ  በቀን እስከ 18 ሚሊዮን የነዳጅ ምርት ለመቀነስ ተስማምተዋል፡፡

እኤአ በ2017 ግንቦት መጀመሪያ ላይ የነዳጅ ዋጋ በ1.3 % በመቀነስ አንድ በርሜል  የድፍድፍ ነዳጅ  ከ49 ዶላር በታች ሲሸጥ እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡

በዚህም  ትላልቅ የነዳጅ አምራች ኩባንያዎችም ለኪሳራ ተዳርገዋል፡፡ ይህ የሆነበት ምክንያት ደግሞ የነዳጅ አምራች ሃገራት የሚያመርቱት የነዳጅ መጠን በመጨመሩ ነው፡፡

 

በነዳጅ ላይ የታየው የዋጋ ግሽፈት ለመቀነስ ደግሞ የነዳጅ አምራችና ላኪ አባል ሃገራትና ሌሎች ነዳጅ አምራች አገራት ስብሰባ አካሂደዋል ፡፡

ቤጂንግ በተደረገው ስብሰባ ሁለቱ ከፍተኛ የነዳጅ አምራች ሃገራት በመሪነት ተሳትፈዋል፡፡ ሳውዲ አረቢያ በመሪነት ከምትመራው የነዳጅ አምራችና ላኪ አባል ሃገራት ድርጅት  (ኦፔክ)ና ሩሲያ የምትመራው ነዳጅ አምራች ሃገራት የተሳተፉበት ውይይት ላይ በቀን ከሚመረተው ድፍድፍ ነዳጅ በአማካይ 1.8 ሚሊዮን በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ ከዚህ አመት አጋማሽ ጀምሮ እስከ ሚቀጥለው  መጋቢት 2018 ድረስ ለመቀነስ ተስማምተዋል፡፡

እንደ ሁለቱም ነዳጅ አምራች ኩባንያ ሚኒስትሮች ስምምነት አሁን የተፈጠረውን የድፍድፍ ነዳጅ የገበያ ዋጋ ግሽፈትን ለማረጋጋትና የተፈለገውን ግብ ለማሳካት የምርት አቅርቦትን መቀነስ ነው፡፡

በዚህም ምናልባት በአማካይ እስከ 5 ዓመታት ሊፈጅ እንደሚችል ተገምቷል፡፡ የድፍድፍ ነዳጅ ገበያው  የተፈለገው ውጤት እስኪገኝ ድረስ ማንኛውንም ነገር ለማድረግ ከስምምነት ደርሰዋል፡፡

የነዳጅ አምራችና ላኪ አባል ሃገራት ኦፔክ በስምምነቱ መሠረት በቀን 1.2 ሚሊዮን በርሜል የነዳጅ ምርት ይቀንሳሉ፡፡

ሩሲያና ሳውዲ አረቢያ በበኩላቸው አለም አቀፍ የነደጅ ፍጆታውን ተመጣጣኝ ለማድረግ አንድ አምስተኛውን በማምረት  በቀን 20 ሚሊዮን በርሜል ማምረት ተስማምተዋል፡፡