ዶክተር ቴድሮስ ኣድሓኖም የመጀመሪያው አፍሪካዊ የዓለም የጤና ድርጅት ዳይሬክተር ጄኔራል ሆኑ

የዓለም ጤና ድርጅት 70ኛውን የዓለም የጤና ጉባዔ በስዊዘርላንድ ጄኔቫ ዛሬ ባካሄደው

ጉባዔ የተገኙ 194 የጤና ሚኒስትሮች አገራት ጤና ድርጅቶች በሰጡት የካርድ ምርጫ ኢትዮጵያዊውን ዶክተር ቴድሮስ ኣድሓኖምን አዲስ የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር እንዲሆኑ 138 ድምጽ መርጧል ፡፡

ኢንግሊዛዊው እና እንግሊዛዊው ዶክተር ዴቪድ ናቫሮ በ45 በመቶ ድምጽ ሲያገኙ ፓኪስታናዊቷ ዶክተር ሳኒያ ኒሺታር በመጀመሪያው ዙር ብቻ በ38 ድምጽ ከውድድር ውጪ መሆናቸው ሆኗል፡፡

ዶክተር ቴድሮስ የተጠቀሙበት የምርጫ ቅስቀሳ መርህም ፍትሃዊ የዓለም የጤና ስርዓት መገንባት የሚያስችልና የብዙ አገራትን ፍላጎትና ጥቅም የሚያስከብር መሆኑም ነው የተገለጸው ፡፡

የቀድሞው የኢፌዲሪ ጤና ጥበቃ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና በአሁኑ ወቅት የጠቅላይ ሚኒስትሩ ልዩ መልዕክተኛ የሆኑት ዶክተር ቴድሮስ ኣድሓኖምን ጨምሮ ሶስቱ እጩዎች ለጉባኤው ንግግራቸውን አቅርበዋል ።

ዶክተር ቴድሮስ ኣድሓኖም በምርጫው ቢያሸንፉ የሰው ልጅን እንደሚያስቀድሙ፣ የጤና ጉዳይ የዓለም ዋነኛ አጀንዳ እንዲሆንና ሃገራት በጤናው ዘርፍ ውጤት የሚያስገኝ ስራ እንዲያከናውኑ ለማድረግ እንደሚጥሩ ነው ያስገነዘቡት ።

ይህም የዓለም ጤና ዋስትና አግኝቶ በበሽታዎች ምክንያቶች የሰው ልጅ ሞት ለመቀነስ እንደሚሰሩ ነው ያረጋገጡት ፡፡

በምዕራብ አፍሪካ ኢቦላ በሽታ ሲከሰት በርካቶች ከሀገራቱ ያላቸውን ግንኙነት የቋረጡበት ሁኔታ የጤና መርህን የጣሰ በመሆኑ እንደሚያስተካክሉ አስታውቀዋል፡፡

ጤና ለሁሉም የሚለው ለምን እንዳልተሳካ በመፈተሽ እንደሚያስተካሉትም እንዲሁ ፡፡

በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ሰዎች የጤና አገልግሎት ማግኘት የሚችሉበትን ዓለም አቀፍ የጤና አገልግሎት ሽፋን እንዲኖር እንደሚያደርጉም አስታውቀዋል።

በሀገራቸው ኢትዮጵያ ተቪ፣ወባና ሌሎች ተላላፊ በሽታዎችን በመከላል ረገድ ውጤታማ ስራ ማከናወናቸውን የጠቀሱት ዶክተር ቴድሮስ ፤አባላት ሀገራቱ የዓለም ጤና ድርጅት እንዲያምኑት ከፍተኛ ጥረት እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል ፡፡

የዓለም የጤና ድርጅትን በተሻለ መልኩ ውጤታማ፣ ግልጽ እና ተጠያቂነት የሰፈነበት ተቋም ለማድረግ እንደሚሰሩም ገልጸዋል።

የጤና ደህንነትን በተመለከተም የመንግስት ባለስልጣናት እና የማህበረሰብ አስተዳደሮችን በሽታን ቀድሞ በመለየት፣ በመከላከል እና አስቸኳይ ስራ የሚያስፈልጋቸው የጤና ጉዳዮች ላይ አቅማቸውን የማጠናከር ስራ ላይ ትኩረት እንደሚሰጡም ገልጸዋል።

ይህም የዓለም ጤና ዋስትና አግኝቶ በበሽታዎች ምክንያቶች የሰው ልጅ ሞት ለመቀነስ እንደሚሰሩ ነው ያረጋገጡት ፡፡

በምዕራብ አፍሪካ ኢቦላ በሽታ ሲከሰት በርካቶች ከሀገራቱ ያላቸውን ግንኙነት የቋረጡበት ሁኔታ የጤና መርህን የጣሰ በመሆኑ እንደሚያስተካክሉ አስታውቀዋል፡፡

ጤና ለሁሉም የሚለው ለምን እንዳልተሳካ በመፈተሽ እንደሚያስተካሉትም እንዲሁ ፡፡

በሀገራቸው ኢትዮጵያ ተቪ፣ወባና ሌሎች ተላላፊ በሽታዎችን በመከላል ረገድ ውጤታማ ስራ ማከናወናቸውን የጠቀሱት ዶክተር ቴድሮስ ፤አባላት ሀገራቱ የዓለም ጤና ድርጅት እንዲያምኑት ከፍተኛ ጥረት እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል ፡፡

ከሀገራትና መንግስታት ጋር በመሆንም የሴቶች፣ የህጻናት እና የወጣቶች የጤና ጉዳይ በዓለም አቀፍ ደረጃ ትኩረት እንዲያገኝ እንሚረባረቡ ነው ያስታወቁት፡፡

ዶክተር ቴድሮስ በእናቶችና ህጻናት ሞት ቅነሳ፣ የወባና የልጅነት ልምሻ በሽታዎችን ከኢትዮጵያ ለመቀነስ ባደረጉት ያላሰለሰ ጥረት በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ተደማጭነትን ማግኘታቸውን ነው የተነገረው  ። 
 

ዶክተር ቴድሮስ እስካሁን በታለፉ የቅድመ ምርጫ ሂደቶች ላይ ሲመሩ መቆየታቸው ይታወቃል ።

ዶክተር ቴድሮስ ለአንድ ዓመት ያክል ከ60 በላይ በሆኑ ሃገራት ባደረጉት ጉብኝት የተሳካ የምርጫ ቅስቀሳ ማድረጋቸውንም እንዲሁ ፡፡ 

በቅስቀሳው አፍሪካ ምርጫውን ማሸነፍ የሚችል የአመራር ብቃትም ሆነ የዓለም ጤና ድርጅትን መለወጥ የሚያስችል ራዕይ ያለው እጩ ማቅረቧን ያሳመነ ስራም መስራታቸውን ነው የተገለጸው :: 

የአፍሪካ፣ ካሪቢያንና ፓሲፊክ ቡድን አባል ሃገሮች ሙሉ በሙሉ ድጋፋቸውን ለዶክተር ቴድሮስ መስጠታቸው የሚታወቅ ነው።

ዶክተር ቴድሮስ በዚህ ምርጫ አሸናፊ በመሆናቸው ለኢትዮጵያ ብሎም ለአፍሪካ እንዲሁም ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ አስቸጋሪ የሆኑትን የዓለም ጤና ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችሉ ሁኔታዎችን ይፈጥራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በዛሬው እለት በስዊዘርላንድ ጄኔቫ ያሸነፉት ዶክተር ቴድሮስ ኣድሓኖም  ከተሰናባቿ የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ማርጋሬት ቻን ስልጣኑን  በይፋ ተረክበዋል ፡፡

በአፍሪካ አዲስ አስደናቂ ታሪክ ያስመዘገቡት ዶክተር ቴድሮስ ኣድሓኖም በቀጣዩ ሐምሌ ወርም የዓለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር በመሆናቸው ስራውን በይፋ የሚጀምሩ ይሆናል።