በትንፋሽ መመርመሪያ መሣሪያ የሚደረገው ቁጥጥር በቂ አይደለም ተባለ

አልኮል ጠጥተው የሚያሽከረክሩ አሽከርካሪዎችን በመመርመሪያ መሣሪያ አማካኝነት  ለመቆጣጣር የሚደረገው እንቅስቃሴ   በቂ  እንዳልሆነ ተገለጸ ።

በአዲስ አበባ ከተማ በትንፋሽ መመርመሪያ መሣሪያ አማካኝነት ጠጥተው የሚያሽከረክሩ አሽከርካሪዎችን  ለመቆጠጣር  የሚደረገው  ጥረት  ጥሩ ቢሆንም  ቁጥጥሩ ግን በቂ እንዳልሆነ አንዳንድ ዋሚኮ  ያነጋገራቸው የአዲስ አበባ  ነዋሪዎች ተናግረዋል ።   

ነዋሪዎቹ  ለዋልታ ቴሌቪዠን በሠጡት አስተያያት እንደገለጹት በትንፋሽ መመርመሪያ የሚደረገው ቁጥጥር  በተወሰኑ  የአዲስ አበባ አካባቢዎችና አልፎ አልፎ የሚደረግ በመሆኑ እየደረሰ ያለውን የትራፊክ አደጋ እንዳልቀነሰው በአዲስ አበባ የሚኖሩ የተለያዩ  የህብረተሰብ  ክፍሎች  ገልጸዋል ።         

ይህንንም ተከትሎ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በበኩሉ እየተደረገ ያለው ቁጥጥር በተገቢው መንገድ እና በበቂ ሆኔታ  መሆኑን ገልፆ ፍተሻው ከተጀመረ በኋላ ከመጠን ያለፈ አልኮል ጠጥተው የሚያሽከረክሩ አሽከርካሪዎች ቁጥር መቀነሱን እና ቅጣቱም ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልፀዋል፡፡

በተያዘው ሩብ አመት 199 አሽከርካሪዎች ከመጠን ያለፈ አልኮል ወስደው የተገኙ እና የተቀጡ ሲሆን ይህም ከአምናው ተመሳሳይ ጊዜ ጋር ሲነጻጻር የቀነሰ መሆኑን ገልፀው የሚደርሰውን  የትራፊክ  አደጋውን ይበልጥ  ለመቀነስ ቁጥጥሩን አጠናክሮ ለመቀጠል እየሰሩ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡