እስራኤል ከ40 ሺህ በላይ ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳናኡጋንዳ ልታዛውር ነው

እስራኤል ከ40 ሺህ በላይ የምስራቅ አፍሪካ ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ እና ኡጋንዳ ልታዘዋውር  መሆኑ   ተገለጸ ፡፡

ድርጊቱ የስደተኞች ፍላጎት ላይ ያልተመሰረተ መሆኑ አሳስቦኛል ብሏል የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን፡፡

የጂውሽ ሰብአዊ መብቶች ቡድን እስራኤል ከ40 ሺህ የሚበልጡና የምጣነ ሃብት ጥገኝነት የሚፈልጉ የአፍሪካ ስደተኞች መልሶ ወደ መጡበት ወይም ለሶስተኛ ሀገራት የመስጠትን እቅድ ይተቻል፡፡

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁ ከሳምንት በፊት 28 አባላት ያሉትን ኮሚቴ ሲያዋቅሩ በሆሎት የሚገኘውን ጊዜያዊ የስደተኞች ማቆያ ካምፕ ለመዝጋት ስለማሰባቸውም ተናግሯል፡፡

ኔታኒያሁ በንግግራቸዉ ስደተኞቹ በ3 ወራት የጊዜ ገደብ ውስጥ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ አስጠንቅቀው ይህ  የማይሆን ከሆነ ግን ስደተኞቹን የእስራኤል መንግስት ለሌላ ሀገር ተላልፎ እንደሚሰጡ አስጠንቅቀውም ነበር፡፡

በአሁን ጊዜ በሀገሪቱ የህግ አዉጪ ተቋም እየታየ ሲሆን የእስራኤል የፀጥታ ጉዳዮችም ስደተኞቹ የተሠጣቸውን ገደብ የማይጠቀሙ ከሆነ እሥር እንደ ሚጠብቃቸው ነው ያሳሰበው፡፡ ከፍተኛ የሀገሪቱ ባለስልጣናትም ድርጊቱ ለእስራኤላዉያን ጥበቃ ለመስጠት ነዉ ሲሉ የጁሽ ሰብአዊ መብቶች ቡድን ግን ድርጊቱ የኢስራኤልን ዴሞክራሲያዊነት በጥያቄ ዉስጥ የሚጥል ብለዉታል፡፡

ራቢ ሚካኤል ሌዛክ የተባለዉ የሀገሪቱ ሰብአዊ መብቶች ተባባሪ ሊቀመንበር ለኒዉስዊክ እንደ ተናገሩት ከኤርትራና ሱዳንን ከመሳሰሉ ሀገራት አስገዳጅ ወታደራዊ አገልግሎት፣ ጭፍጨፋ እና የመንግስታቸዉን ሰብአዊ ወንጀል ሸሽተዉ የሚወጡትን ማረፊያ የለሽ ዜጎች ላይ እንዲ አይነቱን እርምጃ ለመውሰድ መዘጋጀት አስፈሪ መሆኑንም ነው ያሳሰቡት፡፡

ከአፍሪካ ስደተኞች ደግሞ የእቅዱ ተጠቂ ይሆናሉ ተብለው በቁጥር አንድነት የተያዙት የኤርትራ ስደተኞች ናቸዉ፡፡ የኤርትራ ስደተኞች የኢስራኤልን ዲፖርተሸን ፖሊሲ ካሁን በፊትም በተደጋጋሚ ሲተቹ  እንደነበር  ይታወቃል፡፡

የእስራኤል መንግስት እንደሚለው በሀገሪቱ የሚኖሩ የአፍሪካ ስደተኖች ከ40 ሺህ የሚበልጡ ናቸዉ፡፡ ከእነዚህ ውስጥ ደግሞ የኤርትራና የደቡብ ሱዳን ስደተኞች አብላጫዉን ቁጥር የሚይዙ ናቸዉ፡፡

 እስራኤላዉያን የአፍሪካ ጥገኝነት ጠያቂዎች በቴላቪቭ የኑሮን ሁኔታ ከባድ እንዳረጉባቸዉ ይናገራሉ፡፡ አፍሪካዉያኑን ወደ መጡበት የመመለሱ ፖሊሲ በተልአቪቭ የተረጋጋ ሁኔታን ለማስፈን ወሳኝነት አለዉ-።

– የእስራኤሉ የሀገር ዉስጥ ሚኒስትር አሪየህ ዴሪ ለአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ  እንደተናገሩት  የኔ ቀዳሚ ስራ በደቡባዊ ቴላቪቭ እየደፈረሰ የመጣዉን ሰላም እና ፀጥታ መመለስ ይሆናል ብሏል ፡፡

የእስራኤል ባለስልጣናትም ከስደተኞቹ 35ሺዉን የኤርትራና የሱዳን ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ እንደምታዘዋውር ፍቃደኛ ካልሆኑ ደግሞ እስራት እንደሚጠብቃቸው እየገለፁ ያሉት።

ከተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን በተገኘው መረጃም 27 ሺህ 500 ኤርትራውያንና 7ሺህ 800 ሱዳናውያን ስደተኞች ናቸው ከእስራኤል ወደ ሌላ ሀገር የሚዛወሩት።

የሚስራቅ አፍሪካ ስደተኞቹን ወደ ሀገራቸው አሊያም ስደተኞቹን ለመቀበል ፈቃደኛ ወደ ሆኑ ሀገራት ዲፖርት የማድረጉ ወይም የመመለሱ ሁኔታ የጥገኝነት ጥያቄ ያቀረቡ ስደተኞችንም እንደሚመለከት በቴልአቪቭ የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ሻሮን ሐሬል ለቢቢሲ ገልፀዋል።

በተለይ ደግሞ ስደተኞችን ወደ ሶስተኛ ሃገር የማዛወሩ ጉዳይ ለኮሚሽኑ አሳሳቢም እንደሆነ ጨምረው ገልፀዋል።

እነዚህ ስደተኞች በህገ-ወጥ መንገድ ወደ እስራኤል እንደገቡ የሚናገሩት ሻሮን ብዙዎቹም ስደተኞች በግብፅ በኩል ድንበሩን አቋርጠው እንደገቡ ያስረዳሉ። "ብዙ ሴቶች እና ህጻናት መኖራቸው ችግሩን የተወሳሰበ ያደርገዋል" በማለት ሻሮን ይናገራሉ።

ይህ እቅድም ነሐሴ ላይ የእስራኤል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በአውሮፓውያኑ 2015 የእስራኤል መንግሥት አወዛጋቢ የሚባለውን ስደተኞችን በኃይል ወደ ሌላ ሀገር (ሶስተኛ ሃገር) ማዛወር ፓሊሲን መሻሩን ተከትሎ እንደሆነ ኮሚሽኑ በድረ-ገፁ አስታውቋል።

ሻሮን በበኩላቸው ስደተኞቹ በሚደርሱባቸው ሃገራት ደህንነታቸውና መብታቸው እንዲጠበቅ፤ የስራ ፈቃድም እንደሚያገኙ ከእስራኤል ባለስልጣናት በኩል ቃል ቢገባም እንዳልተተገበረ ይናገራሉ።

ፕሮግራሙ ከተተገበረበት ከአውሮፓውያኑ 2013 እስካሁን ባለው 4ሺህ ኤርትራውያንና ሱዳናውያን ስደተኞች መንግሥት "ፈቃድ ያለው መዘዋወር ፕሮግራም" በሚል ወደ ሩዋንዳና ዩጋንዳ ልከዋል።

"የእስራኤል ባለስልጣናት እንደሚሉት ይህ በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ አይደለም" የሚሉት ሻሮን ሳይወዱ በግድ ከእስራኤል ወደ ሶስተኛ ሀገር ከተዘዋወሩ ስደተኞች ባገኙዋቸው የምስክርነት ቃል መረዳት መቻላቸዉን ገልጸዋል፡፡

ከሩዋንዳ በህገ-ወጥ መንገድ ወደ ዩጋንዳ የተወሰዱ፤ ሃገራትን አቆራርጠው ወደ ኩባ የገቡ፤ ከኡጋንዳ ወደ ናይሮቢም በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወሩ ተገኝተው ለእስር የበቁም እንዳሉ ሻሮን ይናገራሉ።

"እነዚህ ስደተኞች በተዛወሩባቸው ሶስተኛ ሃገራት ደህንነት ስላልተሰማቸው ሜድትራንያን ባህርን በአደገኛ ሁኔታ በማቋረጥ ወደ አውሮፓም ሊገቡ የሞከሩ ነበሩ ያሉት ሻሮን የችግሩ መፍትሄ ከኮሚሽኑ አቅምም በላይ መሆኑን ተናግረዋል።

እንደ እስር ቤት የሚታየው የስደተኞች ማቆያ ሆሎት ማዕከል እንዲዘጋ ሰሞኑን ካቢኔቱ ዉሳኔ ማስተላለፉን ተከትሎ በኃይል ስደተኞችን ወደ ሶስተኛ ሃገር የማዛወር ሁኔታም የእሰራኤል ፓርላማ የመጨረሻ ውሳኔ ሰሞኑን ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታኒያሁ ሰሞኑን ቃል እንደ ገቡም ቴልአቪቭ ላይ እስራኤላዉያንን መልሰዉ ለማስፈር ቃል ገብተዋል፡፡ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ግን ስደተኞቹ ሚዛናዊ መሰማት ያሻቸዋል እያሉ ነዉ፡፡

የደቡብ ቴላቪቭ ሁኔታ ሳይጣራ ስደተኞቹ ላይ እርምጃ መወሰድ የለበትም ያሉት ደግሞ የጀዊሽ ሁማኒቴሪል ምክትል ፕሬዝዳንት ማሊን ኔዜር ናቸዉ፡፡ እናም እስራኤል የ1951ዱን የስደተኞች ኮንቨሽን የመጠበቅም ግዴታ አለባት ብሏል ኔዜር፡፡

የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኮሚሽን ሰራተኛን ጠቅሶ እስራኤል የስደተኞችን መብት ስለመገደቧ መስማቱንም አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽን መረጃ እንደሚያመላክትው ባለፉት 9 ዓመታት እስራኤል ከምስራቅ አፍሪካ ስደተኞች በተለይ ደግሞ ከሱዳን እና ኤርትሪ በገፍ ከተሰደዱባት ውስጥ ለ2 ሱዳናዉያን እና 8 ኤርትሪያውያን ብቻ እዉቅና መስጠትዋን ያስረዳል፡፡

ከዳርፉር ወደ ሀገሪቱ የተሰደዱ 200 ሱዳናዉያንም መብቱ የሚገባቸዉ ነበርም ይላል ኮሚሽኑ፡፡

እስራኤል ለእያንዳንዱ ስደተኛ 5ሺህ ዶላር እየከፈለች ስደተኞችን ወደ ሶስተኛ አካል አሳልፋ ለመስጠት ከሩዋንዳ እና ዩጋንዳ ጋር ተስማምቷል፡፡ ይህ የእስራኤል ፖሊሲ ደግሞ የሱዳን እና ኤርትራ ስደተኞችን ክፉኛ የሚጎዳ ነዉ ተብሏል፡፡