በአዲስ አበባ ወሰን ማስከበር በወቅቱ ባለመከናወኑ ለመንገዶች ግንባታ እንቅፋት እየፈጠረ ነው

የመንገድ ወሰን ማስከበር ሥራ ወቅቱን ጠብቆ እየተከናወነ አለመሆኑ ለመንገዶች ግንባታ እንቅፋት መፈጠሩን የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን አስታውቋል፡፡

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከ120 ኪሎ ሜትር በላይ እርዝመት ያለው የመንገድ ግንባታ እያከናወነ ነው፡፡

ባለሥልጣኑ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ውስጥ 76 ኪሎ ሜትር ያህሉን ብቻ ከወሰን ማስከበር ሥራ ነጻ ማድረግ መቻሉን ገልጿል ፡፡

ችግሩን ለመፍታት ባለስልጣን መሥሪያ ቤቱ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን በከተማዋ የሚከናወኑ የመንገድ ፕሮጀክቶች ላይ ያሉ የወሰን ማስከበር ሥራዎችን ወቅቱን ጠብቀው እንዲከናወኑ በቅንጅት እየሠራ እንደሚገኝ ባለሥልጣኑ ያደረሰው መረጃ ያመለክታል፡፡