ኢሚግሬሽን ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር በመተባባር ዘመናዊ የመረጃ ሥርዓት ዘረጋ

ኢሚግሬሽንና ዜግነት ጉዳይ ዋና መምሪያ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር በመተባበር ቀልጣፋ አገልግሎትን ለመሥጠት የሚያስችል  ዘመናዊ የመረጃ  ሥርዓት መዘርጋቱን አስታወቀ ።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት ጉዳይ ዋና መምሪያና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተገልጋዮችን መረጃ ምዝገባ ፣ የክፍያና የቀጠሮ መስጫን የሚቀላጥፍና ደህንነቱ የተጠበቀ ዘመናዊ የመረጃ ስርአት መዘርጋታቸውን አስታውቀዋል፡፡   

ስርአቱ በራስ አቅም መዘጋጀቱ በርካታ ገንዘብ ከወጪ ማዳን ልናድን ችለናል፡፡ አዲሱ ሥርዓት የኢሚግሬሽን አገልግሎት ፈላጊዎችን በተቀላጠፈና በተቀናጀ መልኩ ገንዘባቸውን ፣ ጊዜያቸውንና ጉልበታቸውን እንዲቆጥቡ የሚያስችል ነው፡፡    

ሥርአቱ በአገር አቀፍ ደረጃ ሲተገበር ተገልጋዮች ወደ ኢሚግሬሽን የሚመጡት አሻራ ለመስጠትና ፎቶ ለመነሳት ብቻ ይሆናል ተብሏል፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘ የኢሚግሬሽንና ዜግነት ጉዳይ ዋና መምሪያ ከአዲስ አበባ ውጪ በድሬ ደዋ ፣ ሃዋሳ ፣ ጅማ ፣ ባህር ዳር ፣ ደሴና መቐለ አገልግሎት መስጠት የጀመረ ሲሆን በቅርቡም በጂግጅጋ ፣ አዳማና ሰመራ እንዲሁም በአሶሳ ቢሮ ለመክፈት ዝግጅት ማጠናቀቁ ተገልጻል፡፡