ባለሥልጣኑ በአዲስ አበባ ዙሪያ ለ15ሺህ በላይ ቤተሰቦችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የውሃ መስመር ዘርግቷል

በአዲስ አበባ  ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ከ15 ሺህ በላይ ቤተሰቦችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የውሃ መስመር ዝርጋታ ማከናወኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ገለጸ።

ባለስልጣኑ 31 የመጠጥ ውሃ መስመሮችን በልዩ ዞኑ በሚገኙ አራት ወረዳዎች መዘርጋቱን ጠቅሶ ለሥራውም 79 ሺህ ብር ወጭ መደረጉን ጠቁሟል።

15 ሺህ 552 አባወራዎችና እማወራዎችን ተጠቃሚ ያደርጋሉ የተባለላቸው እነዚህ የውሃ ቦኖዎች በልዩ ዞኑ ውስጥ በመሪኖ፣ በአቃቂ፣ በኤቹና በሰበታ ዙሪያ ደወረ ጉዱ ወረዳዎች የተገነቡ ናቸው።

እነዚህ ወረዳዎች ለረጅም ጊዜ ከፍተኛ የንጹህ መጠጥ ውሃ ችግር የነበረባቸው ሲሆኑ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም ክልሉን ለማገዝ በሚል የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ስራውን ማከናወኑን ባለሥልጣኑ ገልጿል።(ኢዜአ)