ማህበሩ ለተማሪዎቹ የሚያገለግል ከ650 በላይ ገጽ ያለውን መዝገበ ቃላት አስመረቀ

የኦሮሚያ ልማት ማህበር አዳሪ ትምህርት ቤት ለተማሪዎቹ በመማሪያነት የሚያገለግል ከ650 በላይ ገጽ ያለው ከኦሮምኛ ወደ አማርኛ ቋንቋ የሚተረጎም መዝገበ ቃላት ዛሬ አስመርቀዋል፡፡

ልማት ማህበሩ ከአባላት እና ለጋሽ ግለሰቦች በሚያገኘው ድጋፍ የተለያዩ የልማት ስራዎችን እያከናወነ የሚገኝ ሲሆን ከ2006 ዓ.ም ጀምሮ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት በመክፈት ከተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች የተወጣጡ ተማሪዎችን በማስተማር ላይ ይገኛል፡፡

በዛሬው ዕለት በ2010 የትምህርት ዘመን ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ የአዳሪ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የማበረታቻ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ ኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት ወይዘሮ ጣይባ ሀሰን፣ የኦሮሚያ ልማት ማህበር ምክትል የቦርድ ሰብሳቢ ዶክተር ካባ ኡርጌሳ እና የተለያዩ አካላት ተገኝተዋል፡፡