በ110 ሚሊየን ብር የተገነባው የሻሸመኔ ሪፈራል ሆስፒታል ተመረቀ

በ110 ሚሊየን ብር የተገነባው የሻሸመኔ ሪፈራል ሆስፒታል በዛሬው እለት በይፋ ተመርቆ ስራ ጀምሯል።

የሻሸመኔ ሪፈራል ሆስፒታል የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር ወይዘሮ ጠይባ ሀሰን፣ የጤና ሚኒስትር ዶክተር አሚር አማን እና በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ማይክል ሬይነር ጨምሮ ከፍተኛ የፌደራል እና የክልል የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት ነው የተመረቀው።

በዛሬው እለት በይፋ የተመረቀው የሻሸመኔ ሪፈራል ሆስፒታል ህንፃ ከአሜሪካ መንግስት በተገኘ የ110 ሚሊየን ብር ድጋፍ የተሰራ መሆኑም ተነግሯል።

ሆስፒታሉ በአሁኑ ወቅትም አስፈላጊ የህክምና መሳሪያዎች ተሟልተውለት ለአካባቢው ማህበረሰብ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል። (ምንጭ፡-ኤፍ.ቢ.ሲ)