ኢንጅነር ታከለ ኡማ የነዋሪዎች ዲጅታል መታወቂያ አሰጣጥን ጎበኙ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ የነዋሪዎች ዲጅታል መታወቂያ አሰጣጥን ጎበኙ።

ምክትል ከንቲባው ትናንት የተጀመረውን የነዋሪነት ዲጅታል መታወቂያ አሰጣጥ በቦታዉ በመገኘት መመልከታቸውን ነዉ የተገለፀዉ፡፡  

በዚህ ወቅትም ከተገልጋዮች፣ ከባለሙያዎች እና የወረዳ አመራሮች ጋር በአገልግሎት አሰጣጡ ዙሪያ ተነጋግረዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የዲጅታል የነዋሪነት መታወቂያን ከትናንት ጀምሮ መስጠት መጀመሩ ይታወሳል።

ምንጭ ፡- ከአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ፅህፈት ቤት