የጤና ሚኒስቴር ከሀርማወር ሀንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት ጋር ደረጃውን የጠበቀ የምርምር ኢንስቲትዩት ህንጻ ለመገንባት ውል መፈራረማቸዉን ተገለፀ፡፡
በአገሪቱ ሀገር አቀፍ የምርምር ኢንስቲትዩት የመጀመሪያ የሆነው ደረጃውን የጠበቀ እና በ 3 ዓመት ዉስጥ ተጠናቆ አገልግሎት የሚሰጥ ህንጻ ግንባታ ለማስጀመር ውል ተፈርሟል::
የጤና ሚኒስትሩ ዶ/ር አሚር አማን ውሉን ከተፈራረሙ በኋላ የምርምር ተቋሙ ለአገርቱ የጤናው ዘርፍ እድገት የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ በመሆኑ ልዩ ትኩረት ይሰጠዋል ብሏል::
ኮንትራክተሩም ይህንን ከግንዛቤ በማስገባት ህንጻውን በተያዘው ጊዜ በጥራት ሰርተው እንደሚያስረክብ ያላቸውን እምነት ገልጿል::
የህንጻው ግንባታ በሚቀጥለው ሰኞ የቦታ ርክክብ ተፈጽሞ ወደ ግንባታ የሚገባ ሲሆን ለአጠቃላይ ወጪው በመንግስት 526 ሚልዮን ብር ተይዞለታል::
(ምንጭ፡- ጤና ሚኒስቴር)