የሴቶችን ቀን አስመልክቶ ለሶስት ቀናት የሚቆይ ኮንፈረንስ አየተካሄደ ነዉ

በኢትዮጵያ ለ43ኛ ጊዜ ታስቦ የሚውለውን አለም አቀፍ የሴቶች ቀን አስመልክቶ ለሶስት ቀናት የሚቆይ ኮንፈረንስ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

ቀኑ የካቲት 29 ቀን 2011 ዓ.ም ታስቦ የሚውል ሲሆን የሴቶችን ተጠቃሚነትና ተሳታፊነት ለማጎልበት ይጠቅማል ተብሏል፡፡

ኮንፈረንሱን በንግግር የከፈቱት የኢፌዴሪ ሴቶች ህጸናትነና ወጣቶች ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ስመኝ ውቤ ዘንድሮ  በሀገራችን ሴቶች  በውሳኔ ሰጪነት ከፍተኛ ደረጃ ላይ የደረሱበት መሆኑ በአሉን ለየት እንደሚያደርገው ተናግረዋል፡፡

በዓሉም ሴቶችን በስራ እድል ተጠቃሚ ማድረግ፣ የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማሻሻልና ለፌስቱላ ህክምና ትኩረት በመስጠት እየተከበረ መሆኑን አንስተዋል፡፡

መድረኩ በኢፌዴሪ የፋይናንስ፣ ሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ሚኒሰቴር፣ የሲውድን ኤምባሲ፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሴቶች ጉዳይና አለማቀፉ የገንዘብ ድርጅት በጋራ ያዘጋጁት ነው፡፡

ለሶስት ቀናት የሚቆየው ኮንፈራንስ ሴቶች  በማክሮ ኢኮኖሚ ረገድ ያላቸውን ተሳትፎ ለማሻሻል የሚያስችል የፖሊሲ ግበዓት የሚገኝበት መሆኑ ታምኖበታል፡፡የ2011 ዓ.ም ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ወይም ማርች 8 በዓለማቀፍ ደረጃ ለ108ኛ ጊዜ  ታስቦ ይዉላል፡