የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን የተሰሩ የሪፎም ስራዎችን ገምግሟል

የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን ከመጋቢት እስከ መጋቢት የተሰሩ የሪፎም ስራዎችን ገምግሟል፡፡

መስሪያ ቤቶቹ የአደረጃጀት እና የአሰራር ችግር፣ ቴክኖሎጂ ፣ ፖሊሲ የህግ ማእቀፎች እንዲሻሻሉ በማድረግ በአንድ ዓመት ውስጥ ሰፊ ስራዎች መሰራታቸውን ተገልጿል፡፡

በተቋማቱ 33 የሚሆኑ የህጎች እና መመሪያዎች ማሻሻያ ስራዎች መሰራታቸውን ነው የገቢዎች ሚኒስቴር እና ጉምሩክ ኮሚሽን ከፍተኛ የስራ አመራሮች እና የቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቶች ኃፊዎች ባደረጉት ውይይት የተገለጸው፡፡

በህብረተሰቡ ዘንድ ስለ ግብር ግንዛቤ በማሳደግ ደረሰኝ የመስጠት እና የመቀበል ልምድ እንዲኖር የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች መሰራታቸው የገተገለጸ ሲሆን ወደ ፊትም በስፋት መስራት እንደሚያስፈልግም አሳስበዋል፡፡

በውይይቱ የተገኙ የመስሪያ ቤቶቹ የተለያዩ ቅርንጫፎች ሃላፊዎች በበኩላቸው በየቅርንጫፎቹ የሚስተዋሉ በተለይ ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ የሚነሱ ጥያቄዎችን በመቅረፍ ረገድ ሰፊ ስራዎች መሰራታቸውን እና የግብር ስርአቱን ለማዘመንም የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን መጠቀም በጀመራቸውን ነው የገለጹት፡፡

ተቋማቱ በቀጣይም የተዘጋጁ ህጎች እና መመሪያዎችን ለህዝቡ ተደራሽ በማድረግ የግንዛቤ መድረኮችን መፍጠር እንደሚየስል እና የኮንትሮባንድ ቀዉትትር ስራዎችም ተጠናክሮ እንሚቀጥል ተገልጿል፡፡