ጠ/ሚ ዐቢይ በምዕራብ ጉጂ ዞን ወደ መኖሪያቸው የተመለሱ ተፈናቃዮችን እየጎበኙ ነዉ

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በምዕራብ ጉጂ ዞን ቀርጫ ወረዳ ወደ መኖሪያ ቀያቸው የተመለሱ ተፈናቃዮችን እየጎበኙ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምዕራብ ጉጂ ዞን ቀርቻ ወረዳ ጉራቹ ጀልዱ ቀበሌ ወደ መኖሪቸው የተመለሱ ተፋናቃዮችን በቦታዉ ተገኝተዉ አነጋርረዋል፤ የችግኝ ተከላም አከናዉነዋል፡፡

የደቡብ ክልል ርእሰ መስተዳደር አቶ ሚሊዮን ማቲዮስ እና የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል ተፈናቃዮችን እየጎበኙ ይገኛሉ።

በዞኑ ቀርጫ ወረዳ ጉራቹ ጀልዱ ቀበሌ በተለያዩ ግጭቶች ተፈናቅለው የነበሩ ከ3 ሺህ በላይ ነዋሪዎች ወደ መኖሪያቸው ተመልሰዋል።