በሃንጋሪ የጎብኝዎች ጀልባ ሰጥማ የሰባት ሰዎች ሕይወት አለፈ

በሃንጋሪ የጎብኝዎች ጀልባ ሰጥማ የሰባት ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡

በጀልባ መስጠም አደጋው የሰባት ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ የ21 ጎብኚዎች የደረሱበት እንዳልታወቀ ተነግሯል፡፡

ጀልባዋ 30 የደቡብ ኮሪያ ጎብኝዎችን፣ ሶስት አስጎብኝዎችንና ሁለት የጀልበ አገልግሎት ሰራተኞችን አሳፍራ እንደነበረም ነው የተነገረው፡፡

በጀልባዋ ላይ ትናንትና ምሽት የመስጠም አደጋ የደረሰው በሃንጋሪዋ መዲና ቡዳፌስት ዳንዩብ ወንዝ ላይ ከሌላ ትልቅ ጀልባ ጋር ከተጋጨች በኋላ ነው ተብሏል፡፡

በአካባቢው አሁን ላይ ዝናብ እየጣለ ሲሆን÷ ወንዙ በመሙላቱን የነፍስ አድን ስራውን አስቸጋሪ እንዳደረገውም ቢቢሲ በዘገባው ያስረዳል፡፡