ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድና ቀደማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ደም ለገሱ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድና ቀደማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ዓለም ዓቀፍ የደም ልገሳ ቀንን በማስመልከት ደም ለገሱ፡፡
በኢትዮጵያ ለ16ኛ ጊዜ የሚከበረው ዓለም ዓቀፍ የደም ልገሳ ቀንን በማስመልከት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ደም ለግሰዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኅብረተሰቡ በፈቃደኝነት ላይ የተመሠረተ ነፍስ አድን ስጦታ ለማበርከት እንዲሳተፍ ጥሪ ማቅረባቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ባሳለፍነው ሰኔ 7/ 2011 ዓ.ም የተከበረውን የዘንድሮውን ዓለም ዓቀፍ የደም ልገሳ ቀን ሩዋንዳ ማስተናገዷን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡