የኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችል ስትራቴጂክ ዕቅድ አዘጋጀ

የኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ የሚጠበቅበትን አገልግሎት በብቃት ለመስጠት የሚያስችል የ6 ዓመታት ስትራቴጂክ ዕቅድ ማዘጋጀቱን አስታወቀ፡፡   

የዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ብርሃነመስቀል ጠና ከስትራቴጂክ እቅዱ ተጨማሪ የትምህር ክፍሎች ይከፈታሉ፤ ሰፋፊ ግንባታዎች ይከናወናሉ፤ ይህም አሁን ዩኒቨርሲቲዉ ያለዉ 17 ሄክታር መሬት ስለማይበቃ 100 ሄክታር መሬት ያስፈልገናል ብለዋል፡፡
ፕሮጀክቱን ለማከናወን የሚያስችለዉ አጠቃላይ በጀት በተዘጋጀዉ ስትራቴጂክ እቅድ በዝርዝር ቀርቧል፡፡

ስትራተተጂክ እቅድ ተግባራዊ ማድረግ ከተቻለ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተጣለበትን ኃላፊነት በተሟላ መልኩ ለማሳካት ያስችለዋል ነዉ ያሉት ፕሬዝዳንቱ፡፡

ስትራቴጂክ እቅዱ ዙርያ ከቦርድ አመራርና አሰተዳደር ኃላፊነት ጋር ዉይይት የተደረገ ሲሆን አጠቃላይ መግባባት ላይ መድረሳቸዉ ታውቋል፡፡  

ዩኒቨርሲቲዉ በቀጣይ የትምህርት ጥራት ላይ የበለጠ ትኩረት ለመስጠት ማዘጋጀቱንም ተናግረዋል፡፡