የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አባት አረፉ

የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አባት አረፉ

የዶክተር አብይ አህመድ አባት አቶ አህመድ አሊ ባደረባቸው ህመም በጅማ ሆስፒታል በህክምና ሲረዱ ቆይተው ነው ዛሬ ያረፉት ።

የአጋሮ ከተማ አስተዳደር የኮሙኒኬሽን ባለሙያ አቶ ጌታቸው ጎዳና እንደገለጹት፤ አቶ አህመድ አሊ ወይም አባፊጣ አባናሳ ባደረባቸው ህመም በጅማ ሆስፒታል በህክምና ሲረዱ ቆይተው ዛሬ አርፈዋል።

አስከሬናቸውም ዛሬ ወደ አጋሮ-በሻሻ የተወሰደ ሲሆን በነገው እለትም የቀብር ስነ-ስርዓቱ ይፈጸማል ተብሎ እንደሚጠበቅ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።