የግብርና ዘርፉን ለማገዝ የሚያስችሉ በርካታ የመስኖ ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ -ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ

“የዉሃና ኢነርጂ ትራንስፎርሜሽን አዲሲቷ ኢትዮጵያ የተሰፋ አድማስ” በሚል መሪ ቃል  እየተካሄደ ባለው የውይይት መድረክ ላይ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘዉዴ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር የግብርና ዘርፉን ለማገዝ የሚያስችሉ በርካታ የመስኖ ሰራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ ብለዋል፡፡ በአነሰተኛ መስኖ 30 ሺህ ወጣቶችን በማሰማራት ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን አክለዉ ገልጸዋል፡፡

በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ አቅርቦት 97 በመቶ ከታዳሽ ኃይል እንደሚገኝ እና በቀጣይ በታዳሽ ኃይል ዘርፍ እስከ 4 ሚሊየን የሥራ እድል እንደሚፈጠር ይህን ለማጠናከር እንደሚሰራም ተጠቁሟል፡፡

የዉሃ፤ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር የመጀመርያ የዉሃና ኢነርጂ ሳምንት ለማካሄድ ቅድመ ዝግጁቱን ማጠናቀቁንም ገልጿል፡፡  

በኃይል አቅርቦት ለኢንዱስትሪ ፓርኮች 1ሺህ 500 ሜጋዋት የኤሌክትሪክ አቅርቦት የሚያስችል ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡

በመጨረሻም ችግኞችን በመትከል ህብረተሰቡ መረባረብ እንዳለበት ጥሪ ፕሬዝዳንቷ አቅርበዋል፡፡

መርሃግብሩ ከዛሬ ጀምሮ ለሁለት ቀናቶች የሚቆይ ይሆናል፡፡