ናይጄሪያ ከተለያዩ ተቋማት ጋር ያደረገቻቸው ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን ልትሰርዝ ነው

ናይጄሪያ ከተለያዩ ሃገራትና ተቋማት ጋር ያደረገቻቸውን ዓለም አቀፍ ስምምነቶች ልትሰርዝ ነው፡፡  ሃገሪቱ ስምምነቶችን የምትሰርዘው ወጪዋን ለመቀነስ ነው ተብሏል፡፡

ናይጄሪያ ከተለያዩ ሃገራትና ተቋማት ጋር ከ310 በላይ ዓለምቀፍ ስምምነቶችን አድርጋለች፡፡

የሃገሪቱ መንግስት እንዳስታወቀው ከእነዚህ ስምምነቶች ውስጥ አንዳንዶቹ ወጪ የሚያስወጡና የማይጠቅሙ ናቸው ብሏል፡፡

ከእነዚህ ውስጥ 100 የሚሆኑት ስምምነቶች እንደሚሰረዙ ነው የተገለጸው፡፡

የናይጄሪያ መንግስት ስለውሳኔው ሲናገር የአለም አቀፍ ስምምነቶቹ መሰረዝ ሀገሪቱ የምታወጣውን በሚሊዮን ዶላር እንድታድን ያደርጋታል ብሏል፡፡ሲጂቲኤን እንደዘገበው ከሆነ ሃገሪቱ  ለተስማማችባቸው ዓለምዓቀፍ ስምምነቶች ወደ ሰባ ሚሊዮን የሚጠጋ የአሜሪካን ዶላር በዓመት ታወጣለች፡፡

የሃገሪቱ ገንዘብ ሚኒስትር ኪም አዲዮሰን እንደገለጹት ሀገሪቱን ከተለያዩ ድርጅቶች ጋር ካደረገቻቸው ዓለምአቀፍ ስምምነቶች መካከል ካላቸው ጠቀሜታ አንጻር ተገምግመው የሚሰረዙ ይሆናል፡፡

በአሁኑ ወቅትም  መውጣት ያለባቸውን አለም አቀፍ ስምምነቶችን የሚለይ ኮሚቴ መቋቋሙ ታውቋል፡፡

ናይጄሪያ ስምምነቶቹን የተፈራረመችው የነዳጅ ምርቱዋ በተፋፋመበት በቀድሞው አስተዳደር ወቅት ነበር ነገር ግን ከነዳጅ ምርቱ የሚገኘው ገቢ መቀነስ የሀሪቱን ገቢ በ60 በመቶ ዝቅ እንዲል አድርጎታል፡፡

ናይጄሪያ እኤአ በ2015 ፕሬዝዳንት ቡሪ ሀገሪቱ ያደረገቻቸውን የዲፕሎማሲ ግንኙነት  ስምምነቶች ጠቀሜታቸው እንዲጠና አዘው እንደነበር ይታወሳል፡፡

የአለም አቀፍ  ግንኙነቶት ባለሞያ ኢቤንዙር ኦይታኪን ግን "ናይጄሪያ በዚ ውሳኔ ቀዳሚ ትሆናለች በዓለም ዘንድ ያለንን ቦታ አናጣም፣ሀገሪቱ የምትከተለውን ዲፕሎማሲዊ ግንኙነቶችን ከውጪው አለም  ለማጣጣም በሚያስችል ሁኔታ ነው" ብለዋል፡፡

ሀገሪቱ ከምትሰርዛቸው  ስምምነቶች  ምን ያህል ገንዘብ  እንደምታተርፍና ተጽዕኖውስ ምን ሊሆን ይችላል የሚለውን የሚያጠናው ኮሚቴ የጥናቱን ውጤት በቅርቡ እንደሚያቀርብ ይጠበቃል ሲል ሲጅቲኤን ዘግቧል፡፡