ሱዳንና ደቡብ ሱዳን የጋራ ድንበር ጥበቃቸውን ለማቆም ተስማሙ

ሱዳንና ደቡብ ሱዳን ከአምስት ዓመት በላይ ያቋረጡትን በአውሮፕላን የታገዘ የድንበር ጥበቃ  ለማቆም  ተስማሙ ።

ሱዳንና ደቡብ ሱዳን ከአምስት ዓመት በላይ አቋርጠው የቆዩትን በጦር አውሮፕላን የታገዘ የድንበር ጥበቃ ዳግመኛ ለማቆም ተስማምተዋል፡፡ ስምምነቱ በሁለቱም ወገን የሚሞቱ ንጹኃንን መታደግ የሚያስችል  ነው ተብሏል፡፡

ሱዳን እኤአ ነጻነቷን ካወጀችበት የ1956 ጀምሮ የእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ ቆይታለች፡፡ ብዙ እልቂት ያስከተለው ይህ የእርስ በርስ ጦርነት በአለም አቀፉ ማህበረሰብ ግፊት እኤአ በ2005 ላይ በተደረሰ ስምምነት ፈር መያዝ ጀመረ፡፡  

ሁለቱ ሃገራት ማለትም ሱዳንና ደቡብ ሱዳን በህዝበ ውሳኔ ከተለያዩ ጀምሮ ድንበራቸውን በጦር አውሮፕላን የታገዘ የድንበር ላይ ጥበቃ ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡

ይሁን እንጂ ሀገራቱ ይህ በጦር አውሮፕላን የታገዘ የድንበር ጥበቃቸው በሁለቱም ወገን ጉዳት በማስከተሉ  እኤአ በመስከረም 2012 ላይ ለማቋረጥ ተስማምተዋል፡፡

ሁለቱ ሀገራት የተስማሙበት ይህ ማዕቀፍ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውርን መቆጣጠር የሚያስችል፤ለሁለቱም መንግስታት ተቃዋሚዎች ድንበርን በመጠቀም የሚደረግ እርዳታ የሚያስቆም ነው፡፡

በተጨማሪም የሁለቱ ሀገራት ጦር የማይደርሱበት የሰላም ቀጠና እንዲኖርም የሚያስገድድ አንቀፅ አለው፡፡

የአቤይ ሰላም አስከባሪ ቡድን የተካተተበት ሆኖ ሁለቱም ሀገራት ጦር አዋጥተው በጋራ የድንበር ጉዳዮችን እንዲያስተዳድሩም ያዛል፡፡

የደቡብ ሱዳን መንግስት በተፈጠረበት ጥርጣሬ ስምምነቱ ተግባራዊ እንዳይሆን ለ5 ዓመታት አግዶት ቆይቷል፡፡ ጥርጣሬው ደግሞ የሚመሠረተው ነፃ ቀጠና አቋርጦ የሚያልፈው ሁለቱም ሀገራት የኔ ናት በሚሏት አቢዬ ግዛት መሆኑ በዘላቂነት ድንበር ሁኖ ይዘልቃል የሚል ነው፡፡

ጁባ ስጋቷ እያየለ በመምጣቱ ስምምነቱ ተግባራዊ ሊደረግ የቻለው ለአንድ አመት ብቻ ነበር፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአቤዬ ስላም አስከባሪ ባወጣው መግለጫ ካለፈው መስከረም ወር ስምምነቱ እንደአዲስ ተግባራዊ መሆን መጀመሩን አስታውቋል፡፡

ስምምነቱ አሁን ዳግመኛ ተግባራዊ ይሁን እንጂ የተፈረመው ከአምስት አመት በፊት እንደነበር ይታወቃል፡፡

ስለዚህ ከዚህ በኋላ በጦር አውሮፕላን የታገዘው የድንበር ላይ ጥበቃ የተመድ ሰላም አስከባሪው ሆኗል፡፡ ይህም ለሰላም አስከባሪ ኃይሉ ትልቅ እፎይታ ያመጣል ነው የተባለው፡፡ የሁለቱ ሀገራት የጦር ኃይሎች በስምምነቱ መሠረት የጋራ ሥራቸውን መጀመራቸው ተነግሯል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ስምምነቱ ድንበር ዘለል ጥቃቶችን ሊከላከል የሚያስችል በጎ ምግባር ብሎታል፡፡

የአቤይ ሰላም አስከባሪ ቡድን ከምድር እጅግ በቀረበ ከፈታ የሚያደርገው በጦር አውሮፕላን የታገዘ አሰሳው ደግሞ እንቅስቃሴዎችን በቀላሉ ለመቆጣጠር ያስችለዋል ተብሏል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታዉ ምክር ቤት  በአቤዬ ያለውን ሰላም ስከባሪ ቁጥር ከ5ሺ326 ወደ 4ሺ791 ለመቀነስ ባለፈው ግንቦት ወር መወሰኑ ይታወቃል፡፡

ሱዳንና ደቡብ ሱዳን ዳግመኛ ይህን ስምምነት ተግባራዊ እንዲያደርጉ ከስድስት ወር በላይ ውይይት ሲያካሂዱ መቆያታቸውም ታውቋል፡፡ ካርቱምና ጁባ አንዱ ሌላኛውን ከሚከሱባቸው ጉዳዮች ዋንኛው አማጺዎችን መርዳት ነው፡፡ ይህ የአሁኑ ስምምነት የሃገራቱን ድንበር ላይ ውዝግብ ረግበዋል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበታል ሲል ሱዳን ትሪቢዩን ዘግቧል፡፡