የሳሃራ በታች አፍሪካ አገራት 2.9% የኢኮኖሚ እድገት እንደሚያስመዘግቡ የዓለም ባንክ አስታወቀ

በአውሮፓዊያኑ 2019 የሳሃራ በታች የአፍሪካ ሀገራት የ2 ነጥብ 9 በመቶ የኢኮኖሚ እድገት እንደሚያስመዘግቡ የዓለም ባንክ አስታወቀ::

ለኢኮኖሚው እድገት የነዳጅ ምርትና ኤክስፖርት ላይ መሻሻሎች መታየታቸውን፣ የግብርና ምርትና ምርታማነት መነቃቃት መፍጠሩን እና ቀጣይነት ያለው የህዝብ ኢነቨስትመንትን በምክንያትነት ጠቅሷል፡፡

የሃገራቱ የአውሮፓዊያኑ 2020 የኢኮኖሚ እድገትም ወደ 3ነጥብ 3 በመቶ ከፍ እንደሚልም ባንኩ ትንበያውን አስቀምጧል፡፡

ከዚህ እድገት መካከል ደቡብ አፍሪካ በ1ነጥብ 5 በመቶ፣ አንጎላ 2ነጥብ 9 በመቶ እና ናይጀሪያ የ2ነጥብ2 በመቶ ድርሻ እንደሚኖራቸውም ባንኩ በሪፖርቱ አካቷል፡፡

እንደ ሲጂቲኤን ዘገባ የሀገራቱ ሀገራዊ ምርት ላይ እድገት እንደሚመዘገብ የተገለጸ ቢሆንም÷ እድገቱ የቀጠናው ድህነትን ለመቀነዝ በቂ አይደለም፡፡