329 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ አረቢያ ተመለሱ

ግንቦት 18/2013 (ዋልታ) – 329 ኢትዮጵያዊያን ከሳዑዲ አረቢያ ሪያድ ወደ አገራቸው ተመልሰዋል።

ለተመላሾቹ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄኔራል ተወካይ በቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ተገኝተው አቀባበል ማድረጋቸውን ከሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።