የመንግስታቱ ድርጅት በምሥራቅ አፍሪካ ሰላም ለማስፈን በሚደረገው ጥረት ድጋፉን እንዲያጠናክር ተጠየቀ

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 23/2008(ዋኢማ)-በምስራቅ አፍሪካ ዘላቂ ሰላምና ፀጥታ ለማስፈን በሚደረገው ጥረት የመንግስታቱ ድርጅት የሚያደርገውን ድጋፍ እንዲያጠናክር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ቴድሮስ አድሓኖም ጠየቁ።

ዶክተር ቴድሮስ በድርጅቱ የአፍሪካ ፖለቲካ ጉዳዮች ምክትል ዳይሬክተር ሳምባ ሰኔን ትናንት በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

በምስራቅ አፍሪካ የሰላምና የፀጥታ ችግሮች፣የመፍትሄ ሓሳቦችና መወሰድ በሚገባቸው ስትራቴጂ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል።

በአካባቢው በተደጋጋሚ የሚታየውን የሰላምና ፀጥታ ችግር በዘላቂነት ለመፍታት በሚደረገው ጥረት ተመድ የሚያደርገውን የገንዘብና ሌሎች ድጋፎች እንዲያጠናክር ዶክተር ቴድሮስ ጠይቀዋል።

ለግጭት ተጋላጭ አገራት ዋነኛ ምንጭ የሆነው የማህበረሰቡ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት በሚፈለገው መንገድ ባለመሆኑ ድርጅቱ ለፍትሃዊ የልማት ተጠቃሚነት ልዩ ትኩረት መሥጠት ይኖርበታልም ብለዋል።

በመንግስታቱ ድርጅት የአፍሪካ ፖለቲካ ጉዳዮች ምክትል ዳይሬክተር ሳምባ ሳኔ ኢትዮጵያ በሶማሊያ አልሸባብን በመወጋት በደቡብ ሱዳን ተቀናቃኝ ኃይሎች በሰላማዊ መንገድ ችግሮቻቸውን እንዲፈቱ እያደረገች ያለውን ጥረት አድንቀዋል።

ተመድ የቀጠናውን የሰላምና ፀጥታ ችግሮች በዘላቂነት ለመፍታት በሚደረገው ጥረት የገንዘብና ሌሎች ድጋፎችን ያጠናክራል ብለዋል።

ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የደቡብ ሱዳንን ችግር ለመፍታት ተመሳሳይ አቋም ላይ ደርሰዋል በመፍትሄውም ዙሪያ በቀጣይ በጋራ መሥራታቸውን ይቀጥላሉ ብለዋል።

በቀጠናው በጋራ ሰላምና ፀጥታ በማስከበርና ግጭቶችን መፍታት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ትኩረት ሰጥተው ይሰራሉም ብለዋል።

በአካባቢው ለኢኮኖሚያዊ ትስስር ትኩረት በመስጠት የህዝብ ለህዝብ ግኑኝነቱን ማጠናከርና የሰላምና ፀጥታ ችግሮችን መፍታት ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ መሆኑንም ገልጸዋል። (ኢዜአ)