ኢራን 100 ሺህ ሳተላይት ዲሾችን አወደመች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 18/2008 (ዋኢማ)-ኢራን የዜጎቼን አስተሳሰብና ባህል እየቀየረ ነው በሚል 100 ሺህ ሳተላይት ዲሾችንና መቀበያዎችን (ረሲቨሮችን) አወደመች።

በቴህራን በተደረገ ዲሾቹንና መቀበያዎችን የማውደም ስነስርአት ላይ የተገኙት የባሲጅ ሚልሻ ጀነራል መሃመድ ሬዛ ናጊህዲ የሳተላይት ቴሌቪዥኖች ወግ አጥባቂዋ ሀገር ባህል ላይ ተጽእኖ እየፈጠረ ነው ብለዋል።

ጄነራሉ አብዛኞቹ የቴሌቪዥን ቻናሎች ህብረተሰቡ ከባህልና ከሞራል ያፈነገጠ እንዲሆን ማድረጋቸውንና እስካሁን ያስገኙት ውጤትም ፍቺ እንዲበዛ ፣ ሱስ እንዲስፋፋና ህብረተሰቡ የደህንነት ስሜት እንዲያጣ ማድረግ ብቻ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

በሀገሪቱ እስካሁን ከ1 ሚሊየን በላይ ሰዎች በፈቃደኝነት ዲሾችን እና መቀበያዎችን ማስረከባቸውም አክለዋል።

በኢራን ህግ መሰረት የሳተላይት ማስተላለፊያ እቃዎች እገዳ የተጣለባቸው ሲሆን፥ እነዚህን እቃዋች የሚያሰራጩ፣ የሚጠቀሙና የሚጠግኑ 2 ሺህ 800 የአሜሪካ ዶላር ቅጣት ይጣልባቸዋል።

የሀገሪቱ የባህል ሚኒስቴር ህጉ ትክክል ቢሆንም ከ70 በመቶ በላይ የሚሆኑ ኢራናውያን ህጉን ጥሰው እንደሚገኙ ነው ያስተወቀው።

ፕሬዚዳንት ሀሰን ሮሃኒ ግን በሳተላይት ዲሾች ላይ የተጣለው ማዕቀብ ረብ የለሽ መሆኑን በተደጋጋሚ መናገራቸው ተገልጿል።( ኤፍቢሲ)