የኬንያ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በነገው ዕለት ይካሄዳል

ኬንያን በአሁኑ ወቅት እየመሩ ያሉት ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የመጨረሻ የምረጡኝ ቅስቀሳቸውን ለደጋፊዎቻቸው አድርገዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት የፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የቅርብ ተቀናቃኝ እንደሆኑ የሚነገርላቸው ራይላ ኦዴንጋም በተመሳሳይ የምረጡኝ ቅስቀሳቸውን አድርገዋል፡፡

በኬንያን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ምክንያት ከአሁን ቀደም የደረሱ ብጥብጦች ከዘንድሮው ምርጫ በኋላም ይከሰታሉ የሚሉ ስጋቶች ቢያመዝኑም፤ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ግን ችግሩ እንደማይደገም ተስፋ አድርገዋል፡፡

የሀገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን የምርጫ ሂደቱ ነፃና ፍትሃዊ እንዲሆን ለማድረግ የምርጫ ስርዓቱን ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ መንገድ እንደሚካሄድ አስታውቋል፡፡

የምርጫ ውጤት ቅድመ ትንበያን የሚያመላክቱ ጥናቶች እንደሚጠቁሙት ራይላ ኦዲንጋና ፕሬዝዳንት አሁሩ ኬንያታ  የተቀራረበ የምርጫ ውጤት ሊኖራቸው ይችላል፡፡(ምንጭ:ቢቢሲ)